1
መጽሐፈ መክብብ 8:15
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 8:12
ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁ፥
3
መጽሐፈ መክብብ 8:6
የሰው መከራ በእርሱ ላይ እጅግ ስለ ሆነ ለነገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና።
4
መጽሐፈ መክብብ 8:8
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ሥልጣን የለውም፥ በሰልፍም ስንብቻ የለም፥ ኃጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
5
መጽሐፈ መክብብ 8:11
በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይፈረድምና ስለዚህ በሰው ልጆች ውስጥ ልባቸው ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
6
መጽሐፈ መክብብ 8:14
በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኀጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኀጥኣን አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።
7
መጽሐፈ መክብብ 8:7
የሚሆነውንም አያውቅም፥ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው?
Home
Bible
Plans
Videos