1
ትንቢተ ኤርምያስ 17:7-8
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በእግዚአብሔር የሚታመን፥ ተስፋውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኤርምያስ 17:9
“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?
3
ትንቢተ ኤርምያስ 17:10
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
4
ትንቢተ ኤርምያስ 17:5-6
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በሰው የሚታመን የሥጋ ክንዱንም በእርሱ የሚያስደግፍ፥ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚርቅ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንደ አለ ቍጥቋጦ ይሆናል፤ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይኖርበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደረቅ ስፍራ ይቀመጣል።
5
ትንቢተ ኤርምያስ 17:14
አቤቱ! ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤ አንተ መመኪያዬ ነህና።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች