1
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:9
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን” አለው፤ ኤልሳዕም፥ “መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” አለ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:11
ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በሁለቱ መካከል ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ንውጽውጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።
3
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:10
ኤልያስም፥ “አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል፤ ነገር ግን ከአንተ ዘንድ በተወሰድሁ ጊዜ ብታየኝ ይሆንልሃል፤ አለዚያ ግን አይሆንልህም” አለው።
4
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:14
በራሱ ላይ ያረፈችውን የኤልያስን መጠምጠሚያ ወስዶ ውኃውን መታባት፦ ውኃው ግን አልተከፈለም፤ እርሱም፥ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? እንዴትስ ነው?” አለ። ከዚህም በኋላ ውኃውን በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
5
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:12
ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእስራኤል ኀይላቸውና ጽንዓቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ ዳግመኛ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ቀደደው።
6
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:8
ኤልያስም መጠምጠሚያውን ወስዶ ጠቀለለው፤ የዮርዳኖስንም ውኃ መታበት፤ ውኃውም ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ ተሻገሩ። ወጥተውም በምድረ በዳው ቆሙ።
7
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 2:1
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ በሚያወጣው ጊዜ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጌልጌላ ተነሥተው ሄዱ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች