1
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:12
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በመካከላችሁም እመላለሳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:4
ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም የተትረፈረፈ ምርትዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።
3
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:3
“በሥርዓቶቼ ብትመላለሱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉአቸውም፥
4
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:6
በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።
5
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:9
ወደ እናንተም ዘወር ብዬ በበጎ እመለከታችኋለሁ፥ እንድታፈሩም አደርጋችኋለሁ፥ አበዛችሁማለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።
6
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:13
ባርያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ ቀና ብላችሁም እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።”
7
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:11
ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።
8
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:1
“እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለራሳችሁ ይሆኑ ዘንድ ጣዖታትን አትሥሩ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ለእርሱም ለመስገድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
9
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:10
ለብዙም ጊዜ በጎተራ የተቀመጠውን ቀድሞ የነበረውን እህል ትበላላችሁ፤ ለአዲሱም ቦታ ለማስለቀቅ ቀድሞ በጎተራ የነበረውን ታወጣላችሁ።
10
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:8
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም ዓሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በእናንተ ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ።
11
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:5
ለእናተም እህሉን ማበራየቱ የወይኑን ዘለላ እስከሚቆረጥበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፥ የወይኑንም ዘለላ መቁረጥ እህል እስከ ሚዘራበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፤ እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ።
12
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:7
ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በእናንተም ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ።
13
ኦሪት ዘሌዋውያን 26:2
ሰንበታቴን ጠብቁ፥ ለመቅደሴም ክብርን ስጡ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች