1
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:11
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:6-7
እኔስ የመረጥሁት ጾም፥ የበደልን እስራት እንድትፈቱ፥ የቀንበርንስ ጠፍር እንድትለቁ፥ የተገፉትን አርነት እንድታወጡ፥ ቀንበሩን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:8
የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የጌታም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:9
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:10
ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:12
ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የአውራ መንገድ አዳሽ ትባላለህ።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:13-14
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥ በዚያን ጊዜ በጌታ ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ ይህን የጌታ አፍ ተናግሮአልና።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 58:4-5
እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ለማሰማት ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም። እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ?
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች