Free Reading Plans and Devotionals related to ሮሜ 8:37
እግዚአብሔር እኔን የሚወደኝ ለምንድን ነው?
5 ቀናት
ጥያቄዎች: ወደ እግዚአብሔር ሲመጣ ሁላችንም ጥያቄ አለን. በዚህ በንፅፅር የተመሰረተ ባሕላችን ላይ ራሳችንን ሥንጠይቅ የምናገግኘው አንዳንዱ "እግዚአብሔር እኔን የሚወደኝ ለምንድን ነው?" ወይም "እንዴት ሊወደኝ ይችላል?" ይሆናሉ:: በዚህ እቅድ ዉስጥ በጠቅላላው 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ላይ ያቶኩራሉ -- እያንዳንዳቸውም እግዚአብሔር ለእርስዎ ያለዉን ያልተወሰነ ፍቅር እውነታነት ያያሉ::
ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?
11 ቀናት
ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡
BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች
28 ቀናት
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።