1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!” አለ። ራሱን ዘንበል አድርጎም ነፍሱን ሰጠ።
Vergelyk
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:30
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉም ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውም ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ!” አለ።
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:28
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር አጠገቡ ቆመው ባያቸው ጊዜ፥ እናቱን “እናቴ ሆይ! እነሆ፥ ልጅሽ!” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እነኋት እናትህ!” አለው፤ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በሄዱ ጊዜ ግን፥ እርሱ ቀደም ብሎ እንደ ሞተ አይተው፥ ጭኑን አልሰበሩም። ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ፥ ጐኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውኑ ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህም የሆነው፥ “ከእርሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም በሌላው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:17
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት።
Verken የዮሐንስ ወንጌል 19:2
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's