የዮሐንስ ወንጌል 7

7
ኢየሱስ ለበዓል ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ሄደ
1ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በገሊላ ይመላለስ ነበር። አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበር። 2#ዘሌ. 23፥34፤ ዘዳ. 16፥13።የአይሁድም የዳስ በዓል#7፥2 የዳስ በዓል የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከስድስት ወር በኋላ ይከበር ነበር። በዚህ በዓል እስራኤላውያን በበረሃ በነበሩበት ዘመን በድንኳን መኖራቸውን ያስታውሳሉ። ቀርቦ ነበር። 3ወንድሞቹም “ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤ 4በይፋ መታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ እራስህን ለዓለም ግለጥ፤” አሉት። 5ወንድሞቹም እንኳን አላመኑበትም ነበርና። 6ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤ ጊዜያችሁ ግን ዘወትር የተመቸ ነው። 7ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ይጠላኛል፤ ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና ነው። 8እናንተ ወደ በዓሉ ውጡ፤ እኔስ ጊዜዬ ገና ስላልተፈጸመ ወደዚህ በዓል አልወጣም።” 9ይህንም አላቸውና በገሊላ ቀረ።
10ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ፥ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ። 11አይሁድም “እርሱ ወዴት ነው?” እያሉ በበዓሉ ይፈልጉት ነበር። 12በሕዝቡም መካከል በእርሱ ምክንያት ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዶቹ “ደግ ሰው ነው፤” ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ ሕዝቡን ያስታል እንጂ፤” ይሉ ነበር። 13ዳሩ ግን አይሁድን ስለ ፈሩ ማንም ስለ እርሱ በግልጥ አይናገርም ነበር።
ኢየሱስ በዳስ በዓል ላይ ያስተማረው ትምህርት
14በበዓሉ እኩሌታ ኢየሱስ ወደ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ነበር። 15አይሁድም “ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል?” ብለው ይደነቁ ነበር። 16ስለዚህም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ትምህርቴስ የላከኝ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ 17ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንደሆነ ወይንም እኔ ከራሴ የምናገር እንደሆነ ያውቃል። 18ከገዛ እራሱ የሚናገር የገዛ እራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እርሱ እውነተኛ ነው፤ በእርሱም ዐመፃ የለበትም። 19ሙሴ ሕግን አልሰጣችሁምን? ከእናንተ ግን ሕግን የሚፈጽም አንድ እንኳን የለም። ልትገድሉኝ ስለምን ትፈልጋላችሁ?” 20ሕዝቡ መለሱና “ጋኔን አለብህ፤ ማን ሊገድልህ ይፈልጋል?” አሉት። 21ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “አንድ ሥራ ፈጸምኩ፥ ሁላችሁም ትደነቃላችሁ። 22#ዘሌ. 12፥3፤ ዘፍ. 17፥10።ሙሴ መገረዝን#7፥22 የመገረዝን ሥርዓት። ሰጣችሁ፤ ከአባቶችም ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ በሰንበትም ሰውን ትገርዛላችሁ። 23#ዮሐ. 5፥9።የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሰው በሰንበት መገረዝን የሚቀበል ከሆነስ ሰውን ሁለንተናውን በሰንበት ጤናማ ስላደረግሁ ትቈጡኛላችሁን? 24ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ#7፥24 ከሚታየው ተነሥታችሁ አትፍረዱ አትፍረዱ።”
ስለ መሢሑ የተነሣ ክርክር
25ከኢየሩሳሌም ሰዎችም እንዳንዶቹ እንዲህ አሉ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህ አይደለምን? 26እነሆ፥ በግልጥ ይናገራል፤ ነገር ግን ምንም አይሉትም። አለቆቹ ይህ ሰው ክርስቶስ እንደሆነ በእውነት አወቁን? 27ሆኖም ይህ ሰው ከወዴት እንደሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደሆነ ማንም አያውቅም።” 28እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር “እኔንም ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፤ 29እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ፤ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ፤” ብሎ ጮኸ። 30ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም። 31ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበትና፥ “ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ ሰው ካደረጋቸው ምልክቶች የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።
ኢየሱስን እንዲይዙ ወታደሮች መላካቸው
32ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጉሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊይዙት ዘቦችን ላኩ። 33ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ። 34ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤” አለ። 35አይሁድም እንዲህ ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ “እኛ እንዳናገኘው ይህ ሰው ወዴት ሊሄድ ነው? በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሄዶ የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር ነውን? 36‘ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ የሚለውስ ይህ አባባል ምን ማለት ነው?”
ስለ መንፈስ ቅዱስ
37 # ዘሌ. 23፥36። ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። 38#ሕዝ. 47፥1፤ ዘካ. 14፥8።በእኔ የሚያምን፥ መጽሐፍ እንዳለው፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።” 39ይህንንም በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።#7፥39 መንፈስ አልነበረምና ወይም አልተሰጠም ነበርና።
በሕዝቡ መካከል መለያየት መከሠቱ
40ስለዚህ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ በእውነት ነቢዩ#7፥40 ይጠበቅ የነበረው ነቢይ ነው፤” አሉ፤ 41ሌሎች “ይህ ክርስቶስ ነው፤” አሉ፤ ሌሎች ግን “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን? አሉ 42#2ሳሙ. 7፥12፤ ሚክ. 5፥2።ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፥ ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ መጽሐፍ አልተናገረምን?” 43ስለዚህም ከእርሱ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መለያየት ሆነ፤ 44ከእነርሱም አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን እጁን ማንም አልጫነበትም።
45ዘቦቹም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን መጡ፤ እነርሱም “ለምንድነው ያላመጣችሁት?” አሉአቸው። 46ዘቦቹም “እንደዚህ ሰው ማንም ከቶ አልተናገረም፤” ብለው መለሱ። 47ፈሪሳውያንም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፤ “እናንተ ደግሞ ሳታችሁን? 48ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን? 49ነገር ግን ሕግን የማያውቀው ይህ ሕዝብ ርጉም ነው፤” 50#ዮሐ. 3፥1፤2።ከእነርሱ አንዱ በሌሊት ቀድሞ ወደ እርሱ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው 51“ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ፥ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” 52እነርሱም መለሱና “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንደማይነሣ መርምርና እይ፤” አሉት።
53እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።

Айни замон обунашуда:

የዮሐንስ ወንጌል 7: መቅካእኤ

Лаҳзаҳои махсус

Паҳн кунед

Нусха

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in