1
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኢየሱስም “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በሕይወት የሚኖርና በእኔም የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽ?” አላት።
Compare
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የዮሐንስ ወንጌል 11:40
ኢየሱስም “ካመንሽ የእግዚአብሔርን ክብር ታያለሽ ብዬሽ አልነበረምን?” አላት።
የዮሐንስ ወንጌል 11:40ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የዮሐንስ ወንጌል 11:35
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
የዮሐንስ ወንጌል 11:35ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የዮሐንስ ወንጌል 11:4
ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 11:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ “አልዓዛር! ና ውጣ!” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተናገረ። ሟቹ አልዓዛርም እጆቹና እግሮቹ በመገነዣ እንደ ተገነዙ ከመቃብሩ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር፤ ኢየሱስም “ፍቱትና ተዉት ይሂድ!” አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የዮሐንስ ወንጌል 11:38
ኢየሱስ በጣም እያዘነ ወደ መቃብሩ ሄደ፤ መቃብሩ በድንጋይ የተዘጋ ዋሻ ነበር።
የዮሐንስ ወንጌል 11:38ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የዮሐንስ ወንጌል 11:11
ኢየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ፥ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፤ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 11:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ