የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 16

16
በሃ​ይ​ማ​ኖት ስለ መጽ​ናት
1“እን​ዳ​ት​ሰ​ና​ከሉ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። 2ከም​ኵ​ራ​ባ​ቸው ያስ​ወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ ደግ​ሞም እና​ን​ተን የሚ​ገ​ድ​ላ​ችሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​ቀ​ርብ የሚ​መ​ስ​ል​በት ጊዜ ይመ​ጣል። 3ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ችሁ አብ​ንም፥ እኔ​ንም ስላ​ላ​ወቁ ነው። 4ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና። 5አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም። 6ነገር ግን ይህን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ በል​ባ​ችሁ ኀዘን ሞላ።
መን​ፈስ ቅዱ​ስን እን​ደ​ሚ​ል​ክ​ላ​ቸው ተስፋ ስለ​መ​ስ​ጠቱ
7“እኔ በእ​ው​ነት የሚ​ሆ​ነ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ ካል​ሄ​ድሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ ወደ እና​ንተ አይ​መ​ጣ​ምና፤ እኔ ከሄ​ድሁ ግን እር​ሱን እል​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 8እር​ሱም በመጣ ጊዜ ዓለ​ምን ስለ ኀጢ​አ​ትና ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍር​ድም ይዘ​ል​ፈ​ዋል። 9ስለ ኀጢ​ኣት፥ በእኔ አላ​መ​ኑ​ምና ነው፤ 10ስለ ጽድቅ፥ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አታ​ዩ​ኝ​ምና ነው። 11ስለ ፍር​ድም፥ የዚህ ዓለም ገዢ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታ​ልና ነው።
12“የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ብዙ ነገር ነበ​ረኝ፤ ነገር ግን አሁን ልት​ሸ​ከ​ሙት አት​ች​ሉም። 13ያ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እው​ነት ሁሉ ይመ​ራ​ች​ኋል፤ የሚ​ሰ​ማ​ውን ሁሉ ይና​ገ​ራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይ​ና​ገ​ር​ምና፤ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል። 14እር​ሱም እኔን ያከ​ብ​ረ​ኛል፤ ከእኔ ወስዶ ይነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ልና። 15ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለ​ዚ​ህም ከእኔ ወስዶ ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል አል​ኋ​ችሁ።
16“ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።” 17ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድ​ነው?” ተባ​ባሉ። 18“ይህ ጥቂት የሚ​ለን ምን​ድ​ነው? የሚ​ና​ገ​ረ​ውን አና​ው​ቅም” አሉ። 19ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?
ስለ ኀዘ​ንና ስለ ደስታ
20“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ታዝ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ ዓለ​ምም ደስ ይለ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ኀዘ​ና​ችሁ ወደ ደስታ ይለ​ወ​ጣል። 21ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና። 22እና​ን​ተም ዛሬ ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ እን​ደ​ገ​ናም አያ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልባ​ች​ሁም ደስ ይለ​ዋል፤ ደስ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ወ​ስ​ድ​ባ​ችሁ የለም። 23ያን​ጊ​ዜም እኔን የም​ት​ለ​ም​ኑኝ አን​ዳች የለም፤ እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በስሜ አብን ብት​ለ​ም​ኑት ሁሉን ይሰ​ጣ​ች​ኋል። 24እስ​ካ​ሁን ምንም በስሜ አል​ለ​መ​ና​ች​ሁም፤ ደስ​ታ​ችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ ለምኑ፤ ታገ​ኙ​ማ​ላ​ችሁ።
ዓለ​ምን ድል ስለ መን​ሣት
25“ዛሬስ በም​ሳሌ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን የአ​ብን ነገር ገልጬ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ለእ​ና​ንተ በም​ሳሌ የማ​ል​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ይመ​ጣል። 26ያን​ጊዜ በስሜ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም ስለ እና​ንተ አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለህ አል​ላ​ች​ሁም፤ 27እና​ንተ ስለ ወደ​ዳ​ች​ሁኝ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ወጣሁ ስለ አመ​ና​ች​ሁ​ብኝ እርሱ ራሱ አብ ወድ​ዷ​ች​ኋ​ልና። 28ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”
29ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዛሬ ገል​ጠህ ትና​ገ​ራ​ለህ፤ ምንም በም​ሳሌ የተ​ና​ገ​ር​ኸው የለም። 30አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።” 31ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ታም​ና​ላ​ች​ሁን? 32እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ በየ​ቦ​ታዉ የም​ት​በ​ታ​ተ​ኑ​በት፥ እኔ​ንም ብቻ​ዬን የም​ት​ተ​ዉ​በት ጊዜ ይደ​ር​ሳል፤ ደር​ሶ​አ​ልም፤ እኔ ግን ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ አብ ከእኔ ጋር ነውና። 33በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”

Markering

Deel

Kopiëren

None

Wil je jouw markerkingen op al je apparaten opslaan? Meld je aan of log in

Video's voor የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 16