YouVersion လိုဂို
ရှာရန် အိုင်ကွန်

ዘፍጥረት 14

14
አብራም ሎጥን መታደጉ
1አምራፌል የሰናዖር#14፥1 በ9 ላይ ያለውንም ጨምሮ ባቢሎንን ያመላክታል። ንጉሥ፣ አርዮክ የእላሳር ንጉሥ፣ ኮሎዶጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ቲድዓል የጎይም ንጉሥ በነበሩበት ዘመን፣ 2ከሰዶም ንጉሥ ከበላ፣ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ። 3እነዚህ የኋለኞቹ አምስቱ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ፣ በጨው ባሕር#14፥3 የሙት ባሕር ማለት ነው። ተሰበሰቡ። 4እነርሱም ዐሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ከተገዙ በኋላ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ዐመፁ።
5በዐሥራ አራተኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና ከርሱ ጋር የተባበሩት ነገሥታት ወጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኑሚምን በሴዊ ቂርያታይም፣ 6የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይር በረሓማ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ድረስ ድል አደረጓቸው። 7ከዚያም ተመልሰው ዐይን ሚስፖጥ ወደተባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌቃውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ።
8ከዚያም የሰዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ ሰራዊታቸውን አስተባበሩ። 9እነዚህ አምስቱ፣ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉሥ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፣ በእነዚህ በአራቱ ላይ ዘመቱባቸው። 10በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጕድጓዶች ስለ ነበሩ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጕድጓዶች ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራሮች ሸሹ። 11አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በገሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ። 12የአብራም ወንድም ልጅ ሎጥ፣ ሰዶም ይኖር ስለ ነበር እርሱንም ማርከው ንብረቱንም ዘርፈው ሄዱ።
13ከዚህም ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ይህን ነገረ፤ አብራም በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው በአሞራዊው መምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ ነበር። መምሬ፣ ወንድሞቹ#14፥13 ወይም ዘመድ፤ ወይም ጓድ አስኮና አውናን የአብራም የኪዳን አጋሮቹ ነበሩ። 14አብራም የወንድሙን ልጅ መማረክ እንደ ሰማ በቤቱ ተወልደው አድገው የሠለጠኑ 318 ጦረኞች አሰልፎ እስከ ዳን ድረስ ገሠገሠ። 15አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው። 16አብራም ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ የወንድሙን ልጅ ሎጥን፣ ንብረቱን እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎቹን ምርኮኞች አስመለሰ።
17አብራም ኮሎዶጎምርንና አብረውት የተሰለፉትን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ፣ የሰዶም ንጉሥ፣ “የንጉሥ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
18የልዑል እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) ካህን የነበረው የሳሌም#14፥18 ኢየሩሳሌም ናት ንጉሥ መልከጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ 19አብራምንም እንዲህ ሲል ባረከው፤
“ሰማይንና ምድርን የፈጠረ#14፥19 ወይም በ22 ላይ ያለውንም ጨምሮ ባለቤት ሊሆን ይችላል። ልዑል
እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) አብራምን ይባርክ፤
20ጠላቶችህን አሳልፎ በእጅህ የሰጠህ፣
ልዑል እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) ይባረክ።”
አብራምም ካመጣው ሁሉ ዐሥራትን ሰጠው።
21የሰዶም ንጉሥም አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።
22አብራም ግን ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ ወደ ልዑል አምላክ (ኤል-ኤልዮን) እጆቼን አንሥቻለሁ፤ 23‘አብራምን አበለጸግሁት’ እንዳትል፣ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አንዳች አልፈልግም። 24ሰዎቼ ከበሉትና ከእኔ ጋር ከሄዱት ሰዎች ድርሻ በስተቀር ለራሴ አንዳች ነገር አልቀበልም፤ አውናን፣ ኤስኮልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”

လက်ရှိရွေးချယ်ထားမှု

ዘፍጥረት 14: NASV

အရောင်မှတ်ချက်

မျှဝေရန်

ကူးယူ

None

မိမိစက်ကိရိယာအားလုံးတွင် မိမိအရောင်ချယ်သောအရာများကို သိမ်းဆည်းထားလိုပါသလား။ စာရင်းသွင်းပါ (သို့) အကောင့်ဝင်လိုက်ပါ