1
የሐዋርያት ሥራ 1:8
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፥ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮች ትሆኑኛላችሁ።”
နှိုင်းယှဉ်
የሐዋርያት ሥራ 1:8ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የሐዋርያት ሥራ 1:7
እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም።
የሐዋርያት ሥራ 1:7ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የሐዋርያት ሥራ 1:4-5
ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ፥ “ከእኔ የሰማችሁትን የአብን ተስፋ ጠብቁ” ብሎ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው። “ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ፤ እናንተ ግን እስከ ቅርብ ቀን ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” አላቸው።
የሐዋርያት ሥራ 1:4-5ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የሐዋርያት ሥራ 1:3
ሕማማትን ከተቀበለ በኋላ ብዙ ተአምራት በማሳየት አርባ ቀን ሙሉ እየተገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየነገራቸውና እያስተማራቸው ሕያው ሆኖ ራሱንገለጠላቸው።
የሐዋርያት ሥራ 1:3ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የሐዋርያት ሥራ 1:9
ይህንም እየነገራቸው ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ተቀበለችው፤ እነርሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዐይናቸውም ተሰወረ።
የሐዋርያት ሥራ 1:9ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የሐዋርያት ሥራ 1:10-11
እነርሱም ወደ ሰማይ አተኵረው ሲመለከቱ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው። እነርሱም፥ “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየአያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ፥ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” አሏቸው።
የሐዋርያት ሥራ 1:10-11ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
ကျမ်းစာ
အစီအစဉ်
ဗီဒီယို