1
ዘፍጥረት 17:1
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤
ႏွိုင္းယွဥ္
ዘፍጥረት 17:1ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
2
ዘፍጥረት 17:5
ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና።
ዘፍጥረት 17:5ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
3
ዘፍጥረት 17:7
በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ዘፍጥረት 17:7ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
4
ዘፍጥረት 17:4
“እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ።
ዘፍጥረት 17:4ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
5
ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ይሁን ዕሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይሥሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከርሱ ጋራ እገባለሁ።
ዘፍጥረት 17:19ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
6
ዘፍጥረት 17:8
ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።”
ዘፍጥረት 17:8ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
7
ዘፍጥረት 17:17
አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ።
ዘፍጥረት 17:17ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
8
ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሦራን ከእንግዲህ ሦራ ብለህ አትጠራትም፤ ስሟ ከዛሬ ጀምሮ ሣራ ይሁን።
ዘፍጥረት 17:15ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
9
ዘፍጥረት 17:11
ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።
ዘፍጥረት 17:11ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
10
ዘፍጥረት 17:21
ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይሥሐቅ ጋራ አደርጋለሁ።”
ዘፍጥረት 17:21ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
11
ዘፍጥረት 17:12-13
የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ። በቤትህ የተወለደም ሆነ በገንዘብህ የተገዛ ሁሉ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ የሚፈጸመው ይህ ኪዳኔ የዘላለም ኪዳን ይሆናል።
ዘፍጥረት 17:12-13ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
ပင္မစာမ်က္ႏွာ
က်မ္းစာ
အစီအစဥ္
ဗီဒီယို