1
ዘፍጥረት 15:6
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
አብራም እግዚአብሔርን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቈጠረለት።
ႏွိုင္းယွဥ္
ዘፍጥረት 15:6ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
2
ዘፍጥረት 15:1
ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ።”
ዘፍጥረት 15:1ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
3
ዘፍጥረት 15:5
ወደ ውጭም አውጥቶ፣ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስኪ መቍጠር ከቻልህ፣ ከዋክብቱን ቍጠራቸው፤ ዘርህም እንዲሁ ይበዛል” አለው።
ዘፍጥረት 15:5ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
4
ዘፍጥረት 15:4
በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚከፈል ልጅ ወራሽህ ይሆናል።”
ዘፍጥረት 15:4ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
5
ዘፍጥረት 15:13
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ዘርህ በባዕድ አገር መጻተኛ እንደሚሆን በርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመትም በባርነት ተረግጦ ይገዛል።
ዘፍጥረት 15:13ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
6
ዘፍጥረት 15:2
አብራምም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ልጅ የቀረሁ ስለ ሆንሁ፣ የቤቴ ወራሽ የደማስቆ ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” አለው።
ዘፍጥረት 15:2ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
7
ዘፍጥረት 15:18
በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
ዘፍጥረት 15:18ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
8
ዘፍጥረት 15:16
በአራተኛውም ትውልድ ዘርህ ወደዚህ ምድር ይመለሳል፤ የአሞራውያን ኀጢአት ገና ጽዋው አልሞላምና።”
ዘፍጥረት 15:16ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
ပင္မစာမ်က္ႏွာ
က်မ္းစာ
အစီအစဥ္
ဗီဒီယို