ኦሪት ዘፍጥረት 11

11
የባቢሎን ግንብ
1በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩበትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር።#11፥1 ይህ የእግዚአብሔር ትረካ የተለያዩ ሰዎች እና ንግግሮቻቸውን እንዴት እንደተለያየ ገለጣ ይሰጣል፤የኃጢአት መከሰት እና የዚሁ ቅጣት ፍሬ ነው። እርሱም እጅግ በራስ በመተማመን በተፈጠረ ኩራት ኃጢአት ተከሠተ (ቁ. 4) ልክ እንደ ቀድሞው ወላጆቻቸው። አንድነትን በአዳኙ በክርስቶስ ብቻ መመለስ ይቻላል። የጴራቅሊጦስን የልሳን ስጦታ ተመልከት። እንዲሁም በሰማያት የዓለም መንግስት ሁሉ መሰብሰብ። 2ሰዎች ከምሥራቅ ተነሥተው በተጓዙ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፥ በዚያም ተቀመጡ። 3እርስ በርሳቸውም፦ “ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም በደንብ እንተኩሰው” ተባባሉ። በዚህ ዓይነት የሚገነቡትን ጡብ አገኙ፤ በአንድነት የሚያጣብቁበትንም ቅጥራን አገኙ። 4እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ። 5ጌታም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6ጌታም አለ፦ “እነሆ፥ እነዚህ ሕዝቦች አንድ ወገን ናቸው፥ የሁሉም መነጋገሪያ ቋንቋም አንድ ነው። አሁን ይህን ማድረግ ጀመሩ፥ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። 7ስለዚህ ኑ! እንውረድ፥ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” 8ከዚያ በኋላ ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፥ ከተማይቱንም መሥራት አቆሙ። 9ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን#11፥9 እዚህ ላይ “ባቢሎን” ተብሎ የተገለጠው መሰረታዊ ቃል “መደባለቅ” ይባል እንጂ ትክክለኛ ትርጒም “የጣዖት መዝጊያ” ማለት ነው። ተባለ።
ከሴም እስከ አብርሃም
10የሴም ትውልድ ይህ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ሴም መቶ ዓመት በሆነው ጊዜ፥ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ። 11ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ወለደ።
12አርፋክስድም ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሼላሕንም ወለደ፥ 13አርፋክስድም ሼላሕን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ፥ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
14ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፥ 15ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
16ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፥ 17ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
18ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፥ 19ራግውንም ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
20ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፥ 21ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
22ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፥ 23ናኮርንም ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
24ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ፥ 25ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም።
26ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።
የታራ ዘሮች
27የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፥ ሐራንም ሎጥን ወለደ። 28ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። 29አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፥ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፥ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፥ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው። 30ሦራም መካን ነበረች፥ ልጅ አልነበራትም። 31ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ። 32የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፥ ታራም በካራን ሞተ።

Highlight

Kongsi

Salin

None

Ingin menyimpan sorotan merentas semua peranti anda? Mendaftar atau log masuk