የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22

22
የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ጌታን ለመ​ግ​ደል እንደ ፈለጉ
1 # ዘፀ. 12፥1-27። ፋሲ​ካም የሚ​ባ​ለው የቂጣ በዓል ቀረበ። 2የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ይፈ​ሩ​አ​ቸው ነበር።
ይሁዳ ጌታን አሳ​ልፎ ለመ​ስ​ጥት እንደ ተስ​ማማ
3ቍጥሩ ከዐ​ሥራ ሁለቱ በነ​በ​ረው በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ይሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ። 4ሄዶም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከታ​ላ​ላ​ቆች ጋር እር​ሱን አሳ​ልፎ እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ተነ​ጋ​ገረ። 5ደስ ብሏ​ቸ​ውም ሠላሳ ብር#“ሰላሳ ብር” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ሊሰ​ጡት ተስ​ማሙ። 6እር​ሱም እሺ አለ፤ ሰው ሳይ​ኖ​ርም እር​ሱን አሳ​ልፎ ሊሰ​ጣ​ቸው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።
የፋ​ሲ​ካን በግ ስለ ማዘ​ጋ​ጀት
7የፋ​ሲ​ካን በግ የሚ​ያ​ር​ዱ​ባት የቂጣ በዓ​ልም ደረ​ሰች። 8ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስን፥ “ሂዱና የም​ን​በ​ላ​ውን የፋ​ሲካ በግ አዘ​ጋ​ጁ​ልን” አላ​ቸው። 9እነ​ር​ሱም፥ “ወዴት ልና​ዘ​ጋ​ጅ​ልህ ትወ​ዳ​ለህ?” አሉት። 10እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ከተማ በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የውኃ ማድጋ የተ​ሸ​ከመ ሰው ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ሚ​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እር​ሱን ተከ​ተ​ሉት። 11የዚ​ያን ቤት ጌታ፦ መም​ህር ከደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ጋር የፋ​ሲ​ካን በግ የም​በ​ላ​በት ቤት ወዴት ነው? ብሎ​ሃል በሉት። 12እር​ሱም በሰ​ገ​ነት ላይ የተ​ነ​ጠፈ ታላቅ አዳ​ራሽ ያሳ​ያ​ች​ኋል፤ በዚያ አዘ​ጋ​ጁ​ልን።” 13በሄ​ዱም ጊዜ እን​ዳ​ላ​ቸው አገኙ፤ የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ አዘ​ጋጁ።
ስለ ምሥ​ጢረ ቍር​ባን
14ሰዓ​ቱም በደ​ረሰ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጡ። 15እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከመ​ከ​ራዬ አስ​ቀ​ድሞ ይህን ፋሲካ ከእ​ና​ንተ ጋር ልበላ እጅግ ወደ​ድሁ። 16ነገር ግን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ እን​ግ​ዲህ ከእ​ርሱ እን​ደ​ማ​ል​በላ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው። 17ጽዋ​ው​ንም ተቀ​ብሎ አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህን እንኩ ሁላ​ች​ሁም ተካ​ፈ​ሉት። 18እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ክ​ት​መጣ ድረስ፤#በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት አዲ​ሱን እስ​ክ​ጠ​ጣው ድረስ” ይላል። እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከዚህ የወ​ይን ፍሬ አል​ጠ​ጣም።” 19ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤” 20#ኤር. 31፥31-34። እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።
ስለ​ሚ​ያ​ሲ​ዘው ሰው የተ​ሰጠ ምል​ክት
21 # መዝ. 40፥9። “ነገር ግን አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠኝ ሰው እጅ እነሆ፥ በማ​ዕድ ከእኔ ጋር ነው። 22የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በእጁ ለሚ​ሰ​ጥ​በት ለዚያ ሰው ወዮ​ለት።” 23ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ነ​ርሱ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን እንደ ሆነ እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ።
ስለ ትሕ​ትና
24 # ማቴ. 18፥1፤ ማር. 9፥34፤ ሉቃ. 9፥46። ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ነ​ርሱ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ። 25#ማቴ. 20፥25-27፤ ማር. 10፥42-44። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሕ​ዛ​ብን ንጉ​ሦ​ቻ​ቸው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ሥል​ጣን ያላ​ቸው ቸር​ነት አድ​ራ​ጊ​ዎች ይባ​ላሉ። 26#ማቴ. 23፥11፤ ማር. 9፥35። ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ታላቁ እንደ ታናሽ ይሁ​ና​ችሁ፤ አለ​ቃ​ውም እንደ አገ​ል​ጋይ ይሁን። 27#ዮሐ. 13፥12-15። የሚ​በ​ልጥ ማን​ኛው ነው? በማ​ዕድ ላይ የተ​ቀ​መ​ጠው ነው? ወይስ የሚ​ላ​ላ​ከው? በማ​ዕድ ላይ የተ​ቀ​መ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እነሆ፥ እኔ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ አገ​ል​ጋይ ነኝ። 28ነገር ግን ስለ እኔ የታ​ገ​ሣ​ችሁ እና​ንተ በመ​ከ​ራዬ ከእኔ ጋር ናችሁ። 29አባቴ ለእኔ እንደ ሰጠኝ፥ እኔም ለእ​ና​ንተ መን​ግ​ሥ​ትን አዘ​ጋ​ጅ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ 30#ማቴ. 19፥28። በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”
ሃይ​ማ​ኖ​ትን ስለ ማጽ​ናት
31ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ። 32እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።” 33እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እኔ ለመ​ታ​ሰ​ርም ቢሆን፥ ለሞ​ትም ቢሆን እንኳ ከአ​ንተ ጋራ ለመ​ሄድ የተ​ዘ​ጋ​ጀሁ ነኝ” አለው። 34እርሱ ግን፥ “ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ እን​ደ​ማ​ታ​ው​ቀኝ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” አለው። 35#ማቴ. 10፥9-10፤ ማር. 6፥8-9፤ ሉቃ. 9፥3፤ 10፥4። ደግ​ሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረ​ጢ​ትና ያለ ጫማ በላ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ በውኑ የተ​ቸ​ገ​ራ​ች​ሁት ነገር ነበ​ርን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት። 36እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮ​ጆ​ውን ይያዝ፤ ከረ​ጢ​ትም ያለው እን​ዲሁ ያድ​ርግ፤ ሰይፍ የሌ​ለ​ውም ልብ​ሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። 37#ኢሳ. 53፥12። እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ተቈ​ጠረ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው በእኔ ይደ​ር​ሳል፤ ስለ እኔ የተ​ጻ​ፈ​ውም ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል።” 38እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆ፥ እዚህ በእኛ ዘንድ ሁለት ሰይ​ፎች አሉ” አሉት፤ እር​ሱም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ ይበ​ቃ​ች​ኋል” አላ​ቸው።
በደ​ብረ ዘይት ስለ መጸ​ለዩ
39ወጥ​ቶም እን​ዳ​ስ​ለ​መ​ደው ይጸ​ልይ ዘንድ#“ይጸ​ልይ ዘንድ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ወደ ደብረ ዘይት ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ተከ​ተ​ሉት። 40ከዚ​ያም ደርሶ፥ “ወደ መከራ እን​ዳ​ት​ገቡ ጸልዩ” አላ​ቸው። 41የድ​ን​ጋይ ውር​ወራ ያህ​ልም ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብሎ እየ​ሰ​ገደ ጸለየ። 42እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባት ሆይ፥ ብት​ፈ​ቅ​ድስ ይህን ጽዋ ከእኔ አሳ​ል​ፈው፤ ነገር ግን የአ​ንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይ​ሁን።” 43የሚ​ያ​በ​ረ​ታ​ታው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ታየው። 44ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ። 45ከሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሄደ፤ ከኀ​ዘ​ንም የተ​ነሣ ተኝ​ተው አገ​ኛ​ቸው። 46“ስለ ምን ትተ​ኛ​ላ​ችሁ? ወደ ፈተና እን​ዳ​ት​ገቡ ተነ​ሡና ጸልዩ” አላ​ቸው።
በአ​ይ​ሁድ እጅ ስለ መግ​ባቱ
47ይህ​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው ሕዝቡ ደረሱ፤ ከዐ​ሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ ይሁ​ዳም ይመ​ራ​ቸው ነበር፤ ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቀርቦ ሳመው፤ የሰ​ጣ​ቸ​ውም ምል​ክት ይህ ነበር፤ “የም​ስ​መው እርሱ ነውና እር​ሱን አጽ​ን​ታ​ችሁ ያዙት”#“የም​ስ​መው እርሱ ነውና እር​ሱን አጽ​ን​ታ​ችሁ ያዙት” የሚ​ለው በግ​ሪ​ኩና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። አላ​ቸው። 48ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይሁ​ዳን፥ “በመ​ሳም የሰ​ውን ልጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለ​ህን?” አለው። 49አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩ​ትም የሆ​ነ​ውን ባዩ ጊዜ፥ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “አቤቱ፥ በሰ​ይፍ ልን​መ​ታ​ቸው ትፈ​ቅ​ዳ​ለ​ህን?” አሉት። 50ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ የሊቀ ካህ​ና​ቱን አገ​ል​ጋይ መታው፤ ቀኝ ጆሮ​ው​ንም ቈረ​ጠው። 51ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ​ንስ ተው” አለ፤ ወዲ​ያ​ውም ጆሮ​ውን ዳስሶ አዳ​ነው። 52ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊይ​ዙት ወደ እርሱ የመ​ጡ​ትን የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችን፥ የቤተ መቅ​ደስ ሹሞ​ች​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሌባን እን​ደ​ም​ት​ይዙ በሰ​ይ​ፍና በጎ​መድ ልት​ይ​ዙኝ መጣ​ች​ሁን? 53#ሉቃ. 19፥47፤ 21፥37። ዘወ​ት​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር በቤተ መቅ​ደስ ስኖር እጃ​ች​ሁን እንኳ አል​ዘ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብ​ኝም፤ ነገር ግን ጊዜ​ያ​ችሁ ይህ ነው፤ የጨ​ለ​ማው አበ​ጋ​ዝም ሥል​ጣኑ ይህ ነው።”
ስለ ጴጥ​ሮስ ክሕ​ደት
54ይዘ​ውም ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ቤት ወሰ​ዱት፤ ጴጥ​ሮ​ስም ከሩቅ ይከ​ተ​ለው ነበር። 55በግ​ቢ​ውም ውስጥ እሳት አን​ድ​ደው ተቀ​መጡ፤ ጴጥ​ሮ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጠ። 56በእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና አየ​ችው፤ እርሱ መሆ​ኑ​ንም ለየ​ች​ውና፥ “ይህም ከእ​ርሱ ጋር ነበር” አለች። 57እርሱ ግን፥ “ሴትዮ! የም​ት​ዪ​ውን አላ​ው​ቅም” ብሎ ካደ። 58ከጥ​ቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አየ​ውና፥ “አን​ተም ከእ​ነ​ርሱ ወገን ነህ” አለው፤ ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም” አለው። 59አን​ዲት ሰዓት ያህ​ልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእ​ው​ነት ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ሰው​የ​ውም የገ​ሊላ ሰው ነው” ብሎ አስ​ጨ​ነ​ቀው። 60ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ። 61ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ። 62ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።
አይ​ሁድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ላይ ስለ መዘ​ባ​በ​ታ​ቸው
63ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘ​ውት የነ​በ​ሩት ሰዎ​ችም ይዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትና ይደ​በ​ድ​ቡት ነበር። 64ሸፍ​ነ​ውም ፊቱን በጥፊ ይመ​ቱት ነበር፤ “ፊት​ህን በጥፊ የመ​ታህ ማነው? ንገ​ረን” እያ​ሉም ይጠ​ይ​ቁት ነበር። 65ሌላም ብዙ ነገር እየ​ተ​ሳ​ደቡ በእ​ርሱ ላይ ይና​ገሩ ነበር።
በአ​ደ​ባ​ባይ ስለ መቆሙ
66በነ​ጋም ጊዜ፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ወሰ​ዱት። 67“አንተ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ በግ​ልጥ ንገ​ረን” አሉት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብነ​ግ​ራ​ች​ሁም አታ​ም​ኑ​ኝም። 68ብጠ​ይ​ቃ​ች​ሁም አት​መ​ል​ሱ​ል​ኝም፤ ወይም አት​ተ​ዉ​ኝም። 69ነገር ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ቀኝ ይቀ​መ​ጣል።” 70ሁሉም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነህን?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆንሁ እና​ንተ ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው። 71እነ​ር​ሱም፥ “ስለ እርሱ ምን ምስ​ክር እን​ሻ​ለን? እኛ ራሳ​ችን ሲና​ገር ሰም​ተ​ናል” አሉ።

Ընդգծել

Կիսվել

Պատճենել

None

Ցանկանու՞մ եք պահպանել ձեր նշումները ձեր բոլոր սարքերում: Գրանցվեք կամ մուտք գործեք