ኦሪት ዘፍጥረት 2
2
1ሰማይና ምድር ዓለማቸውም ሁሉ ተፈጸሙ። 2እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በስድስተኛው ቀን ፈጸመ፤ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። 3እግዚአብሔር ሰባተኛዋን ቀን ባረካት፤ ቀደሳትም፤ ሊፈጥረው ከጀመረው ሥራ ሁሉ በእርስዋ ዐርፎአልና።
4እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ፍጥረት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰማይና የምድር የልደት መጽሐፍ ነው” ይላል። ይህ ነው። 5የሜዳ ቍጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ አዳምም ከመፈጠሩ በፊት፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አዳም ከመፈጠሩ በፊት” አይልም። እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም። 6ነገር ግን የውኃ ምንጭ ከምድር ይወጣ ነበር፤ የምድርንም ፊት ሁሉ ያጠጣ ነበር። 7እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
አዳም በኤዶም ገነት
8እግዚአብሔር አምላክም በኤዶም በስተምሥራቅ ገነትን ተከለ፤ የፈጠረውንም ሰው በዚያ አኖረው። 9እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያሳየውንና የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። 10ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤዶም#በግእዙ “ኤዶም” አይልም። ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለዐራት መዓዝን ይከፈል ነበር። 11የአንደኛው ወንዝ ስም ኤፌሶን#በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. “ፊሶን” ይላል። ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል። 12የዚያችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። 13በዚያም የሚያበራ ዕንቍና የሚያብረቀርቅ ዕንቍ አለ። የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፤ 14የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሶር ላይ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። 15እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም፥ ይጠብቃትም ዘንድ በኤዶም ገነት አኖረው። 16እግዚአብሔር አምላክም አዳምን እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ 17ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
18እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።” 19እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ደግሞ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደጠራው ስሙ ያው ሆነ። 20አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣ፤ አንቀላፋም ፤ ከጎኑም አጥንቶች አንድ አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ መላው። 22እግዚአብሔር አምላክም#ምዕ. 2 ቁ. 4፥ 5፥ 6፥ 7፥ 8፥ 9፥ 10፥ 15፥ 16 ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግዚአብሔር አምላክ” ሲሉ፤ ግእዙ “እግዚአብሔር” ብቻ ይላል። ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። 23ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋዋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከባልዋ ተገኝታለችና ሚስት ትሁነኝ።”#በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. “እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” ይላል። 24ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ሚስቱንም ይከተላል ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25አዳምና ሚስቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር።
હાલમાં પસંદ કરેલ:
ኦሪት ዘፍጥረት 2: አማ2000
Highlight
શેર કરો
નકલ કરો
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in