የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 1

1
ስለ ቃል ቀዳ​ማ​ዊ​ነት
1በመ​ጀ​መ​ሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነበረ። 2ይህም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበረ። 3ሁሉም በእ​ርሱ ሆነ፤ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም። 4ሕይ​ወት በእ​ርሱ ነበረ፥ ሕይ​ወ​ትም የሰው ብር​ሃን ነበረ፤ 5ብር​ሃ​ንም በጨ​ለማ ያበ​ራል፤ ጨለ​ማም አላ​ገ​ኘ​ውም።
ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ መላክ
6 # ማቴ. 3፥1፤ ማር. 1፥4፤ ሉቃ. 3፥1-2። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ላከ ስሙ ዮሐ​ንስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር። 7እር​ሱም ሁሉ በእ​ርሱ በኩል እን​ዲ​ያ​ምን ስለ ብር​ሃን ይመ​ሰ​ክር ዘንድ ለም​ስ​ክ​ር​ነት መጣ። 8ስለ ብር​ሃን ምስ​ክር ሊሆን መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብር​ሃን አል​ነ​በ​ረም።
9ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው። 10በዓ​ለም ነበረ፤ ዓለ​ሙም በእ​ርሱ ሆነ፤ ዓለሙ ግን አላ​ወ​ቀ​ውም። 11ወደ ወገ​ኖቹ መጣ፤ ወገ​ኖቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም። 12ለተ​ቀ​በ​ሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚ​ያ​ምኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ዲ​ሆኑ ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው። 13እነ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተወ​ለዱ እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ግብር ወይም ከወ​ን​ድና ከሴት#“ከሴት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እኛ በአ​ብ​ዛ​ኛው የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ፈቃድ አል​ተ​ወ​ለ​ዱም።
ቃል ሥጋ ስለ​መ​ሆኑ
14ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው። 15ምስ​ክሩ ዮሐ​ንስ ስለ እርሱ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ ስለ እርሱ ከእኔ በፊት የነ​በረ ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ያል​ኋ​ችሁ ሰው ይህ ነው፥ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ረና።” 16እኛም ሁላ​ችን ከሙ​ላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀ​በ​ልን። 17ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን። 18በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።
ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት
19አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው። 20እር​ሱም፥ “እኔ ክር​ስ​ቶስ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ አመነ እንጂ አል​ካ​ደም። 21#ዘዳ. 18፥15፤ 18፤ ሚል. 4፥5። “እን​ኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤል​ያስ ነህን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ “አይ​ደ​ለ​ሁም” አለ፤ “እን​ኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይ​ደ​ለ​ሁም” አለ። 22“እን​ኪ​ያስ አንተ ማነህ? ለላ​ኩ​ንም መልስ እን​ድ​ን​ሰጥ ስለ ራስህ ማን ትላ​ለህ?” አሉት። 23#ኢሳ. 40፥3። እር​ሱም፥ “ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ እያለ በም​ድረ በዳ የሚ​ሰ​ብክ የዐ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ። 24የተ​ላ​ኩ​ትም ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ነበሩ። 25“እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶ​ስን ካል​ሆ​ንህ፥ ኤል​ያ​ስ​ንም ካል​ሆ​ንህ፥ ነቢ​ይ​ንም ካል​ሆ​ንህ ለምን ታጠ​ም​ቃ​ለህ?” ብለው ጠየ​ቁት። 26ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤#በግ​ሪኩ “አጠ​ም​ቃ​ለሁ” ይላል። ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ቆሞ​አል። 27ከእኔ በኋላ የሚ​መ​ጣው፥ ከእኔ በፊት የነ​በ​ረው፥ የጫ​ማ​ውን ጠፍር ልፈታ እንኳ የማ​ይ​ገ​ባኝ ነው።”#“እርሱ ግን በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስና በእ​ሳት ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል” የሚል በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ ይገ​ኛል። 28ዮሐ​ንስ ያጠ​ም​ቅ​በት በነ​በ​ረው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በቢ​ታ​ንያ በቤተ ራባ እን​ዲህ ሆነ።
29በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ። 30ከእኔ በፊት የነ​በረ ሰው ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ብዬ ስለ እርሱ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ይህ ነው፤ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ርና። 31እኔ አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ያ​ው​ቁት ስለ​ዚህ እኔ በውኃ ላጠ​ምቅ መጣሁ።” 32ዮሐ​ን​ስም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ከሰ​ማይ እንደ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀ​መጥ አየሁ። 33እኔም አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን በውኃ እን​ዳ​ጠ​ምቅ የላ​ከኝ እርሱ መን​ፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀ​መ​ጥ​በት የም​ታ​የው በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ያ​ጠ​ምቅ እርሱ ነው አለኝ። 34እኔም ራሴ አይ​ቻ​ለሁ፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።”
ስለ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዎቹ ደቀ መዛ​ሙ​ርት
35በማ​ግ​ሥ​ቱም ደግሞ ዮሐ​ንስ ከሁ​ለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፥ 36ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ሲሄድ አይቶ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ#“የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ሰ​ወ​ግድ ...” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ” አለ። 37ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ ሲል ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ተከ​ተ​ሉት። 38ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ሲከ​ተ​ሉት አየና፥ “ምን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው። 39እነ​ር​ሱም፥ “ረቢ፥ ትር​ጓ​ሜ​ውም መም​ህር ሆይ፥ ማለት ነው፤ ወዴት ትኖ​ራ​ለህ?” አሉት። 40እር​ሱም “መጥ​ታ​ችሁ እዩ” አላ​ቸው፤ ሄደ​ውም የሚ​ኖ​ር​በ​ትን አዩ፤ ያን ዕለ​ትም እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ በእ​ርሱ ዘንድ ዋሉ። 41ከዮ​ሐ​ንስ ዘንድ ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከሁ​ለ​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ ነበር። 42እር​ሱም መጀ​መ​ሪያ ወን​ድሙ ስም​ዖ​ንን አግ​ኝቶ “በት​ር​ጓ​ሜው ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲ​ሕን አገ​ኘ​ነው” አለው። 43እር​ሱም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ወሰ​ደው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስም​ዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባ​ላ​ለህ፤” አለው፤ ትር​ጓ​ሜ​ውም ጴጥ​ሮስ ማለት ነው።
ስለ ፊል​ጶ​ስና ስለ ናት​ና​ኤል
44በማ​ግ​ሥ​ቱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ወደደ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም አገ​ኘ​ውና “ተከ​ተ​ለኝ” አለው። 45ፊል​ጶስ ግን ከእ​ን​ድ​ር​ያ​ስና ከጴ​ጥ​ሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር። 46ፊል​ጶ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን አገ​ኘ​ውና፥ “ሙሴ በኦ​ሪት፥ ነቢ​ያ​ትም ስለ እርሱ የጻ​ፉ​ለ​ትን የዮ​ሴ​ፍን ልጅ የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን አገ​ኘ​ነው” አለው። 47ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በውኑ ከና​ዝ​ሬት ደግ ሰው#በግ​ሪኩ “መል​ካም ነገር” ይላል። ሊወጣ ይቻ​ላ​ልን?” አለው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “መጥ​ተህ እይ” አለው። 48ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተን​ኰል የሌ​ለ​በት እው​ነ​ተኛ እስ​ራ​ኤ​ላዊ ይህ ነው” አለ። 49ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው። 50ናት​ና​ኤ​ልም መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ በእ​ው​ነት አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አንተ ነህ” አለው። 51#ዘፍ. 28፥12። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “በበ​ለስ ዛፍ ሥር አየ​ሁህ ስለ አል​ሁህ አመ​ን​ህን? ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ታያ​ለህ” አለው። 52“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሰማ​ያት ሲከ​ፈቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ወደ ሰው ልጅ ሲወ​ር​ዱና ሲወጡ ታያ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید