1
ኦሪት ዘፍጥረት 4:7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በበርህ ላይ ያደባል፤ በቊጥጥሩ ሥር ሊያደርግህም ይፈልጋል፤ ሆኖም አንተ ልታሸንፈው ይገባል።”
مقایسه
ኦሪት ዘፍጥረት 4:7 را جستجو کنید
2
ኦሪት ዘፍጥረት 4:26
ሤትም “ሄኖስ” የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የጀመሩት በዚያን ጊዜ ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት 4:26 را جستجو کنید
3
ኦሪት ዘፍጥረት 4:9
እግዚአብሔርም ቃየልን “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤ ቃየልም “የት እንዳለ አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ብሎ መለሰ።
ኦሪት ዘፍጥረት 4:9 را جستجو کنید
4
ኦሪት ዘፍጥረት 4:10
እግዚአብሔርም ቃየልን እንዲህ አለው፤ “ምን አደረግህ? የፈሰሰው የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው፤
ኦሪት ዘፍጥረት 4:10 را جستجو کنید
5
ኦሪት ዘፍጥረት 4:15
እግዚአብሔር ግን “ማንም አይነካህም፤ አንተን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ስለዚህ እግዚአብሔር ቃየልን ማንም ቢያገኘው እንዳይገድለው የሚያስጠነቅቅ ልዩ ምልክት አደረገለት።
ኦሪት ዘፍጥረት 4:15 را جستجو کنید
خانه
كتاب مقدس
برنامههای مطالعه
ویدیوها