1
ዘፍጥረት 4:7
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”
مقایسه
ዘፍጥረት 4:7 را جستجو کنید
2
ዘፍጥረት 4:26
ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም መጥራት ጀመሩ።
ዘፍጥረት 4:26 را جستجو کنید
3
ዘፍጥረት 4:9
ከዚያም፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ቃየንን፣ “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው። ቃየንም፣ “አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ሲል መለሰ።
ዘፍጥረት 4:9 را جستجو کنید
4
ዘፍጥረት 4:10
እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “ምንድን ነው ያደረግኸው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።
ዘፍጥረት 4:10 را جستجو کنید
5
ዘፍጥረት 4:15
እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን፣ “የለም! እንደርሱ አይሆንም፤ ማንም ቃየንን ቢገድል፣ ሰባት ዕጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው፤ ስለዚህ፣ ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው እግዚአብሔር (ያህዌ) በቃየን ላይ ምልክት አደረገለት።
ዘፍጥረት 4:15 را جستجو کنید
خانه
كتابمقدس
برنامههای مطالعه
ویدیوها