YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 11

11
የሰ​ና​ዖር ግንብ
1የዓ​ለም ሁሉ ቋንቋ አንድ፥ ንግ​ግ​ሩም አንድ ነበረ። 2እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከም​ሥ​ራ​ቅም ተነ​ሥ​ተው በሄዱ ጊዜ በሰ​ና​ዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ። 3እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ጡብ እን​ሥራ፤ በእ​ሳ​ትም እን​ተ​ኵ​ሰው” ተባ​ባሉ። ጡባ​ቸ​ውም እንደ ድን​ጋይ፥ ጭቃ​ቸ​ውም እንደ ዝፍት ሆነ​ላ​ቸው። 4እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ልጆች የሠ​ሩ​ትን ከተ​ማና ግንብ ለማ​የት ወረደ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ እነ​ርሱ አንድ ወገን ናቸው፤ ለሁ​ሉም አንድ ቋንቋ አላ​ቸው፤ ይህ​ንም ለማ​ድ​ረግ ጀመሩ፤ አሁ​ንም ያሰ​ቡ​ትን ሁሉ መሥ​ራ​ትን አይ​ተ​ዉም። 7ኑ እን​ው​ረድ፤ አንዱ የሌ​ላ​ውን ነገር እን​ዳ​ይ​ሰ​ማው ቋን​ቋ​ቸ​ውን በዚያ እን​ደ​ባ​ል​ቀው።” 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቋን​ቋ​ቸ​ውን ለያየ፤#“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቋን​ቋ​ቸ​ውን ለያየ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከዚ​ያም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ በተ​ና​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና ግን​ቡን መሥ​ራ​ትን ተዉ። 9ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ባቢ​ሎን ተባለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ የም​ድ​ርን ቋንቋ ሁሉ ደባ​ል​ቆ​አ​ልና፤ ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ሁሉ ፊት ላይ እነ​ር​ሱን በት​ኖ​አ​ቸ​ዋል።
የሴም ትው​ልድ
(1ዜ.መ. 1፥24-27)
10የሴም ትው​ልድ ይህ ነው። ሴም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት አር​ፋ​ክ​ስ​ድን በወ​ለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበረ። 11ሴምም አር​ፋ​ክ​ስ​ድን ከወ​ለደ በኋላ አም​ስት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
12አር​ፋ​ክ​ስ​ድም መቶ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ቃይ​ና​ን​ንም ወለደ፤ 13አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ አርባ ዓመት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አራት መቶ ሠላሳ” ዕብ. “አራት መቶ” ይላል። ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይ​ና​ንም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ሳላ​ንም ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ#ዕብ. “ሦስት መቶ ሠላሳ” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ልጆች ወለደ፤ ሞተም።
14ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ዔቦ​ር​ንም ወለደ፤ 15ሳላም ዔቦ​ርን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ ሊ. “ሦስት መቶ ሠላሳ” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
16ዔቦ​ርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፤ ፋሌ​ቅ​ንም ወለደ፤ 17ዔቦ​ርም ፋሌ​ቅን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሦስት መቶ ሰባ” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
18ፋሌ​ቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ራግ​ው​ንም ወለደ፤ 19ፋሌ​ቅም ራግ​ውን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
20ራግ​ውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሴሮ​ሕ​ንም ወለደ፤ 21ራግ​ውም ሴሮ​ሕን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
22ሴሮ​ሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ናኮ​ር​ንም ወለደ፤ 23ሴሮ​ሕም ናኮ​ርን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
24ናኮ​ርም መቶ ዘጠኝ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሰባ ዘጠኝ” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ታራ​ንም ወለደ፤ 25ታራ​ንም ከወ​ለደ በኋላ ናኮር መቶ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።
የታራ ትው​ልድ
26ታራም መቶ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰባ” ይላል። ዓመት ኖረ፥ አብ​ራ​ም​ንና ናኮ​ርን፥ አራ​ን​ንም ወለደ። 27አራ​ንም ሎጥን ወለደ።#ዕብ. “የታ​ራም ትው​ልድ ይህ ነው ታራ አብ​ራ​ም​ንና ናኮ​ርን፥ አራ​ን​ንም ወለደ” ይላል። 28አራ​ንም በተ​ወ​ለ​ደ​ባት ሀገር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር#ዕብ. “ዑር” ይላል። በአ​ባቱ በታራ ፊት ሞተ። 29አብ​ራ​ምና ናኮ​ርም ሚስ​ቶ​ችን አገቡ፤ የአ​ብ​ራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የና​ኮ​ርም ሚስት የአ​ራን ልጅ ሚልካ ናት፤ አራ​ንም የሚ​ል​ካና የዮ​ስካ አባት ነው። 30ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም። 31ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ። 32ታራም በካ​ራን ምድር የኖ​ረ​በት ዘመን ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካ​ራን ሞተ።

Tõsta esile

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in