ኦሪት ዘፍጥረት 10
10
የኖኅ ልጆች ትውልድ
(1ዜ.መ. 1፥5-23)
1የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካምና፥ የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
የያፌት ትውልድ
2የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። 3የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። 4የይህያንም ልጆች ኤልሳ፥ ተርሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ#ዕብ. “ዶዳኒም” ይላል። ናቸው። 5ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።
የካም ትውልድ
6የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምስራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው። 7የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ሬጌም፥ ሰበቅታ ናቸው። የሬጌም ልጆችም ሳባ፥ ዮድዳን ናቸው። 8ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኀያል መሆን ጀመረ። 9እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኀያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ኀያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። 10የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር ሀገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካሌድን ናቸው። 11አሦርም ከዚያች ሀገር ወጣ፤ ነነዌን፥ ረሆቦት የተባለችውን ከተማ ካለህን፥ 12በነነዌና በካለህ መካከልም ዳስን#ዕብ. “ሬሴን” ይላል። ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት። 13ምስራይምም ሉዲምን፥ ኢኒሜቲምን፥ ላህቢምን፥ ንፍታሌምን፥ ጳጥሮሶኒምን፥ 14ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሎሂምንና ቀፍቶሪምንም ወለደ።
15ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጤዎንን፥ 16ኢያቡሴዎንን፥ አሞሬዎንን፥ ጌርጌሴዎንን፥ 17ኤዌዎንን፥ አሩቄዎንን፥ ኤሴኒዎንን፥ 18አራዲዎንን፥ ሰማርዮንን፥ አማቲንን#ዕብ. ምዕ. 10 ከቍ. 15 እስከ 18 ያለውን በብዙ ቍጥር ይጽፋል። ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። 19የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል። 20የካም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
የሴም ትውልድ
21ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነው ነው። 22የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይናን።#“ቃይናን” በግእዙ እና በዕብ. የለም። 23የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጋቴር፥ ሞሳሕ ናቸው። 24አርፋክስድም ቃይናንን ወለደ፤ ቃይናንም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ። 25ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው። 26ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሳሌፍንም፥ ሐሰረሞትንም፥ ያራሕንም፥ 27ሀዶራምንም፥ አዚላንም፥#በግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤቤል” በዕብ. “አውዛል” ይላል። ደቅላንም፥ 28ዖባልንም፥ አቤማኤልንም፥ ሳባንም፥ 29አፌርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዮባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው። 30ስፍራቸውም ከማሲ አንስቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው። 31የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
32የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከእነዚህም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ ተዘሩ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 10: አማ2000
Tõsta esile
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in