Logo de YouVersion
Ícono Búsqueda

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 13

13
የአ​ብ​ራ​ምና ሎጥ መለ​ያ​የት
1አብ​ራ​ምም ከግ​ብፅ ወጣ፤ እር​ሱና ሚስቱ፥ ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ፥ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። 2አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ። 3ከአ​ዜብ ባደ​ረ​ገው በጕ​ዞ​ውም ወደ ቤቴል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስ​ቀ​ድሞ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል ድን​ኳን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረው ነው፤ 4ስፍ​ራ​ውም አስ​ቀ​ድሞ መሠ​ውያ የሠ​ራ​በት ነው፤ በዚ​ያም አብ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ። 5ከአ​ብ​ራም ጋር የሄ​ደው ሎጥ ደግሞ የላ​ምና የበግ መንጋ ድን​ኳ​ኖ​ችም ነበ​ሩት። 6በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቸ​ውም፤ ንብ​ረ​ታ​ቸው ብዙ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚ​ህም ባን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቻ​ቸ​ውም። 7በአ​ብ​ራ​ምና በሎጥ መን​ጎች ጠባ​ቆች መካ​ከ​ልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና ፌር​ዛ​ው​ያን በዚ​ያች ምድር ተቀ​ም​ጠው ነበር። 8አብ​ራ​ምም ሎጥን አለው፥ “እኛ ወን​ድ​ማ​ማች ነንና በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በእ​ረ​ኞ​ቼና በእ​ረ​ኞ​ችህ መካ​ከል ጠብ አይ​ሁን። 9እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብት​ሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አን​ተም ወደ ቀኙ ብት​ሄድ እኔ ወደ ግራ እሄ​ዳ​ለሁ።” 10ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ። 11ሎጥም ለራሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥ​ራቅ ተጓዘ፤ አን​ዱም ከሌ​ላው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ። 12አብ​ራም በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ፤ ሎጥም በጎ​ረ​ቤት ሕዝ​ቦች ከተማ ተቀ​መጠ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም በሰ​ዶም ተከለ፤#ግእዙ “ወደ ሰዶም ተጓዘ” ይላል። 13የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ።
አብ​ራም ወደ ኬብ​ሮን እንደ ሄደ
14ሎጥ ከተ​ለ​የው በኋ​ላም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዐይ​ን​ህን አን​ሣና አንተ ካለ​ህ​በት ስፍራ ወደ መስ​ዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ምዕ​ራብ እይ፤ 15የም​ታ​ያ​ትን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና። 16ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “እንደ ምድር አሸዋ” ይላል። አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል። 17ተነሣ፤ በም​ድር በር​ዝ​መ​ቷም፥ በስ​ፋ​ቷም ዙር፤ እር​ስ​ዋን ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።” 18አብ​ራ​ምም ድን​ኳ​ኑን ነቀለ፤ መጥ​ቶም በኬ​ብ​ሮን ባለው የመ​ምሬ ዛፍ ተቀ​መጠ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ።

Destacar

Compartir

Copiar

None

¿Quieres guardar tus resaltados en todos tus dispositivos? Regístrate o Inicia sesión