1
የዮሐንስ ወንጌል 16:33
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
Σύγκριση
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 16:33
2
የዮሐንስ ወንጌል 16:13
ያ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 16:13
3
የዮሐንስ ወንጌል 16:24
እስካሁን ምንም በስሜ አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ ለምኑ፤ ታገኙማላችሁ።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 16:24
4
የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
“እኔ በእውነት የሚሆነውን እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም በመጣ ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአትና ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍርድም ይዘልፈዋል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
5
የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
እናንተም ዛሬ ታዝናላችሁ፤ እንደገናም አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። ያንጊዜም እኔን የምትለምኑኝ አንዳች የለም፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በስሜ አብን ብትለምኑት ሁሉን ይሰጣችኋል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
6
የዮሐንስ ወንጌል 16:20
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፤ ዓለምም ደስ ይለዋል፤ እናንተ ግን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 16:20
Αρχική
Αγία Γραφή
Σχέδια
Βίντεο