1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ ቅርንጫፎቹም እናንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉምና።
Σύγκριση
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:5
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ከአልኖረ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል እናንተም እንዲሁ በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:4
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔም ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የምትሹትን ሁሉ ትለምናላችሁ፤ ይደረግላችሁማል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:7
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:16
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:13
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:2
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
“እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድቷደዱ የእኔ ትእዛዝ ይህች ናት።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:12
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ብታፈሩ፥ ደቀ መዛሙርቴም ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:8
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካዩም አባቴ ነው።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:1
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጥሉታል፤ ሰብስበውም በእሳት ያቃጥሉታል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:6
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ደስታዬ በእናንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስታችሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገርኋችሁ።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:11
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
የምትወዱኝ ብትሆኑ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ፥ በፍቅሩም እንደምኖር እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:10
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እርስ በርሳችሁም እንድቷደዱ ይህን አዝዣችኋለሁ።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:17
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
እናንተስ ከዓለም ብትሆኑ ዓለም በወደዳችሁ ነበር፤ ዓለም ወገኖቹን ይወዳልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ ከዓለም አይደላችሁምና ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።
Διαβάστε የዮሐንስ ወንጌል 15:19
Αρχική
Αγία Γραφή
Σχέδια
Βίντεο