Logo YouVersion
Ikona vyhledávání

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 9

9
ስለ ሐዋ​ር​ያት መላክ
1ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ሐዋ​ር​ያት ጠራና፦ በአ​ጋ​ን​ንት ሁሉ ላይ፥ ድው​ያ​ን​ንም ይፈ​ውሱ ዘንድ ኀይ​ል​ንና ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው። 2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እን​ዲ​ሰ​ብኩ፥ ድው​ያ​ን​ንና ሕሙ​ማ​ን​ንም ሁሉ እን​ዲ​ፈ​ውሱ ላካ​ቸው። 3#ሉቃ. 10፥4-11፤ የሐዋ. 13፥51። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በት​ርም ቢሆን፥ ከረ​ጢ​ትም ቢሆን፥ እን​ጀ​ራም ቢሆን፥ ወር​ቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብ​ስም ቢሆን ለመ​ን​ገድ ምንም አት​ያዙ። 4በም​ት​ገ​ቡ​በት ቤት በዚያ ተቀ​መጡ፤ እስ​ክ​ት​ሄ​ዱም ድረስ ከዚያ አት​ውጡ።#አን​ዳ​ንድ ዘርዕ “ከዚ​ያም ዉጡ” ይላል። 5የማ​ይ​ቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ቢሆን ግን ከዚ​ያች ከተማ ወጥ​ታ​ችሁ ምስ​ክር ሊሆ​ን​ባ​ቸው የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ።” 6ወጥ​ተ​ውም በየ​አ​ው​ራ​ጃዉ መን​ደ​ሮች ዞሩ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም ሁሉ ወን​ጌ​ልን ሰበኩ፤ ድው​ያ​ን​ንም ፈወሱ።
ስለ ሄሮ​ድስ ዐሳብ
7የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዥ ሄሮ​ድ​ስም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ሰምቶ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ያጣ ነበር፤ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነሣ የሚሉ ነበ​ሩና። 8#ማቴ. 16፥14፤ ማር. 8፥28፤ ሉቃ. 9፥19። ኤል​ያስ ተገ​ለጠ የሚ​ሉም ነበሩ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉም ነበ​ሩና። 9ሄሮ​ድ​ስም፥ “እኔ የዮ​ሐ​ን​ስን ራስ አስ​ቈ​ረ​ጥሁ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ እርሱ ሲወራ የም​ሰ​ማው ይህ ማነው?” አለ፤ ሊያ​የ​ውም ይሻ ነበር።
10ሐዋ​ር​ያ​ትም በተ​መ​ለሱ ጊዜ ያደ​ረ​ጉ​ትን ሁሉ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው ይዞ​አ​ቸው ቤተ ሳይዳ ከም​ት​ባል ከተማ አጠ​ገብ ወደ አለ ምድረ በዳ ወጡ። 11ሕዝ​ቡም ዐው​ቀው ተከ​ተ​ሉት፤ እር​ሱም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ሊፈ​ወሱ የሚ​ሹ​ት​ንም አዳ​ና​ቸው።
ኅብ​ስ​ትን ስለ ማበ​ር​ከቱ
12ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት መጥ​ተው፥ “ያለ​ን​በት ምድረ በዳ ነውና በዙ​ሪ​ያ​ችን ወዳሉ መን​ደ​ሮ​ችና ገጠ​ሮች ሄደው እን​ዲ​ያ​ድሩ የሚ​በ​ሉ​ት​ንም እን​ዲ​ያ​ገኙ ሕዝ​ቡን አሰ​ና​ብት” አሉት። 13እርሱ ግን፥ “እና​ንተ የሚ​በ​ሉ​ትን ስጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚ​በቃ ምግብ ልን​ገዛ ካል​ሄ​ድን ከአ​ም​ስት እን​ጀ​ራና ከሁ​ለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለ​ንም” አሉት። 14ሰዎ​ቹም አም​ስት ሺህ ያህሉ ነበር፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም፥ “አምሳ አም​ሳ​ውን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አስ​ቀ​ም​ጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው። 15እን​ዲ​ሁም አደ​ረጉ፤ ሁሉም ተቀ​መጡ። 16አም​ስ​ቱን እን​ጀ​ራና ሁለ​ቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመ​ለ​ከተ፤ ባረከ፤ ቈር​ሶም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ያ​ቀ​ርቡ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው። 17ሁሉም በል​ተው ጠገቡ፤ ያነ​ሡ​ትም የተ​ረ​ፈው ቍር​ስ​ራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።
ሰው ማን ይለ​ኛል? ብሎ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ስለ መጠ​የቁ።
18ከዚ​ህም በኋላ ብቻ​ውን ሲጸ​ልይ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ሳሉ፥ “ሰዎች ማን ይሉ​ኛል?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው። 19#ማቴ. 14፥1-2፤ ማር. 6፥14-15፤ ሉቃ. 9፥7-8። እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ነው የሚ​ሉህ አሉ፤ ኤል​ያስ ነው የሚ​ሉ​ህም አሉ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉ​ህም አሉ” አሉት። 20#ዮሐ. 6፥68-69። እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ማን ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው፤ ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሲሕ ነህ” አለው። 21ይህ​ንም ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ ገሠ​ጻ​ቸ​ውና ከለ​ከ​ላ​ቸው።
ስለ ሕማ​ሙና ስለ​ሚ​ከ​ተ​ሉት የተ​ና​ገ​ረው
22“ለሰው ልጅ ብዙ መከራ ያጸ​ኑ​በት ዘንድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችም ይፈ​ት​ኑት ዘንድ፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ፥ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነሣ ዘንድ አለው” አላ​ቸው። 23#ማቴ. 10፥38፤ ሉቃ. 14፥27። ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሊከ​ተ​ለኝ የሚ​ወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክ​ኖም የሞ​ቱን መስ​ቀል ይሸ​ከም፤ ዕለት ዕለ​ትም ይከ​ተ​ለኝ። 24#ማቴ. 10፥39፤ ሉቃ. 17፥33፤ ዮሐ. 12፥25። ሰው​ነ​ቱን ሊያ​ድን የሚ​ወድ ሁሉ ይጥ​ላ​ታል፤ ስለ እኔ ሰው​ነ​ቱን የጣለ ግን ያድ​ና​ታል። 25ሰው ዓለ​ሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍ​ሱ​ንም ካጣ ምን ይረ​ባ​ዋል? 26በእ​ኔና በቃሌ የሚ​ያ​ፍር ሁሉ የሰው ልጅ በክ​ብሩ፥ በአ​ባ​ቱም ክብር፥ ቅዱ​ሳ​ን​መ​ላ​እ​ክ​ትን አስ​ከ​ትሎ ሲመጣ ያፍ​ር​በ​ታል። 27እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚህ ከቆ​ሙት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ያ​ዩ​አት ድረስ ሞትን የማ​ይ​ቀ​ምሱ አሉ።”
በደ​ብረ ታቦር ክብ​ሩን ስለ መግ​ለጡ
28ከዚ​ህም ነገር በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ጴጥ​ሮ​ስን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዮሐ​ን​ስን ይዞ​አ​ቸው ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ። 29ሲጸ​ል​ይም የፊቱ መልክ ተለ​ወጠ፤ ልብ​ሱም ነጭ ሆነ፤ እንደ መብ​ረ​ቅም አብ​ለ​ጨ​ለጨ። 30እነ​ሆም፥ ሁለት ሰዎች መጥ​ተው ከእ​ርሱ ጋር ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። እነ​ር​ሱም ሙሴና ኤል​ያስ ነበሩ። 31በክ​ብ​ርም ተገ​ል​ጠው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይደ​ረግ ዘንድ ያለ​ውን ክብ​ሩ​ንና#በግ​ሪኩ “ክብ​ሩን ...” አይ​ልም። መው​ጣ​ቱን ተና​ገሩ፤ 32ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ት​ንም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው በእ​ን​ቅ​ልፍ ፈዝ​ዘው አገኘ፤ በነ​ቁም ጊዜ ክብ​ሩ​ንና ከእ​ርሱ ጋር ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት ሰዎች አዩ። 33ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ርሱ ሲለዩ ጴጥ​ሮስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “መም​ህር፥ ሆይ፥ እዚህ ብን​ኖር ለእኛ መል​ካም ነው፤ ሦስት ሰቀ​ላ​ዎ​ች​ንም እን​ሥራ፤ አን​ዱን ለአ​ንተ፥ አን​ዱ​ንም ለሙሴ፥ አን​ዱ​ንም ለኤ​ል​ያስ” አለው፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቅም ነበር። 34ይህ​ንም ሲና​ገር ደመና መጣና ጋረ​ዳ​ቸው፤ ወደ ደመ​ና​ውም በገቡ ጊዜ ፈሩ። 35#ኢሳ. 42፥1፤ ማቴ. 3፥17፤ 12፥18፤ ማር. 1፥11፤ ሉቃ. 3፥22። ከደ​መ​ና​ውም ውስጥ፥ “የመ​ረ​ጥ​ሁት ልጄ ይህ ነው፤ እር​ሱን ስሙት” የሚል ቃል መጣ። 36ቃሉም ከመጣ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ብቻ​ውን ተገኘ፤ እነ​ርሱ ግን ዝም አሉ፤ ያዩ​ት​ንና የሰ​ሙ​ት​ንም በዚያ ጊዜ ለማ​ንም አል​ተ​ና​ገ​ሩም።
ጋኔን ይጥ​ለው የነ​በ​ረ​ውን ስለ ማዳኑ
37በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ራ​ራው ወረዱ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ተቀ​በ​ሉት። 38አንድ ሰውም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጮኾ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ እርሱ ለእኔ አንድ ነውና ልጄን ታይ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ። 39እነሆ፥ ጋኔን ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው፤#“ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ አይ​ገ​ኝም። ድን​ገ​ትም ያስ​ጮ​ኸ​ዋል፤ ጥሎም ያፈ​ራ​ግ​ጠ​ዋል፤ አረ​ፋም ያስ​ደ​ፍ​ቀ​ዋል፤ ቀጥ​ቅጦ በጭ​ንቅ ይተ​ወ​ዋል። 40እን​ዲ​ያ​ወ​ጡ​ትም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ለመ​ን​ሁ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው።” 41ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “የማ​ታ​ምን ከዳ​ተኛ ትው​ልድ፥ እስከ መቼ ከእ​ና​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼስ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ? ልጅ​ህን ወደ​ዚህ አም​ጣው” አለው። 42ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።
ስለ ሕማሙ
43እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው። 44“እና​ን​ተስ ይህን ነገር በል​ባ​ችሁ#በግ​ሪኩ “በጆ​ሮ​አ​ችሁ አኑ​ሩት” ይላል። አኑ​ሩት፤ የሰው ልጅ በሰ​ዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለ​ውና።” 45እነ​ርሱ ግን ይህን ነገር አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ እን​ዳ​ይ​መ​ረ​ም​ሩት ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነውና፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም እን​ዳ​ይ​ጠ​ይ​ቁት ይፈ​ሩት ነበ​ርና።
ስለ ትሕ​ትና
46 # ሉቃ. 22፥24። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ ዐሰቡ። 47ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በል​ቡ​ና​ቸው የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና አንድ ሕፃን ወስዶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አቆ​መው። 48#ማቴ. 10፥40፤ ሉቃ. 10፥16፤ ዮሐ. 13፥20። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በስሜ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሕፃን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፥ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል፤ ራሱን ከሁሉ#በግ​ሪኩ “ከሁ​ላ​ችሁ የሚ​ያ​ንስ እርሱ ታላቅ ይሆ​ናል” ይላል። ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ እርሱ ታላቅ ይሆ​ናል።”
49ዮሐ​ን​ስም መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ በስ​ምህ ጋኔን ሲያ​ወጣ ያየ​ነው አንድ ሰው አለ፤ ከእ​ኛም ጋር አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ህ​ምና ከለ​ከ​ል​ነው፤” አለው። 50ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ከ​ል​ክ​ሉት፤ ባለ​ጋ​ራ​ችሁ ካል​ሆነ ባል​ን​ጀ​ራ​ችሁ#በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ከእ​ና​ንተ ጋር ነውና” ይላል። ነውና” አላ​ቸው። 51የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና። 52በፊ​ቱም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ሄደ​ውም ያዘ​ጋ​ጁ​ለት ዘንድ ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ገቡ። 53ነገር ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም፤ ፊቱን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅ​ንቶ ነበ​ርና። 54#2ነገ. 1፥9-16። ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ን​ስም ይህን ባዩ ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ኤል​ያስ እንደ አደ​ረገ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ ያጥ​ፋ​ቸው እን​ድ​ንል ትፈ​ቅ​ዳ​ለ​ህን?” አሉት። 55እርሱ ግን ዘወር ብሎ፥ “ከምን መን​ፈስ እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁም” ብሎ ገሠ​ጻ​ቸው። 56የሰው ልጅ የሰ​ውን ነፍስ ሊያ​ድን እንጂ ሊያ​ጠፋ አል​መ​ጣም። ወደ ሌላም መን​ደር ሄዱ።
ሊከ​ተ​ሉት ስለ ጠየ​ቁት ሰዎች
57ከዚህ በኋላ በመ​ን​ገድ ሲሄዱ አንድ ሰው፥ “መም​ህር፥ ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በት ልከ​ተ​ል​ህን?” አለው። 58ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም “ለቀ​በ​ሮ​ዎች ጕድ​ጓድ አላ​ቸው፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ጎጆ አላ​ቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚ​ያ​ስ​ጠ​ጋ​በት የለ​ውም” አለው። 59ሌላ​ው​ንም፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው፤ እርሱ ግን፥ “አቤቱ፥ በፊት ሄጄ አባ​ቴን እን​ድ​ቀ​ብ​ረው ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው። 60ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ዘንድ ሙታ​ንን ተዉ​አ​ቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ስበክ” አለው። 61#1ነገ. 19፥20። ሦስ​ተ​ኛ​ውም፥ “አቤቱ፥ ልከ​ተ​ል​ህን? ነገር ግን ሄጄ ቤተ ሰቦ​ችን ሁሉ እን​ድ​ሰ​ና​በት ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው። 62ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማንም ዕርፍ ይዞ እያ​ረሰ ወደ ኋላው የሚ​መ​ለ​ከት#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ዕርፍ ይዞ ወደ​ኋላ የሚ​ያ​ርስ የለም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የቀ​ናች ናትና” ይላል። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የተ​ገባ አይ​ሆ​ንም” አለው።

Zvýraznění

Sdílet

Kopírovat

None

Chceš mít své zvýrazněné verše uložené na všech zařízeních? Zaregistruj se nebo se přihlas

Videa pro የሉ​ቃስ ወን​ጌል 9