የሉቃስ ወንጌል 20
20
ከሊቃነ ካህናት የቀረበ ጥያቄ
1ከዚህም በኋላ በአንድ ቀን ሕዝቡን በመቅደስ ሲያስተምራቸው፥ ወንጌልንም ሲነግራቸው፥ የካህናት አለቆች፥ ጻፎችና ሽማግሌዎች ተነሡበት። 2“ይህን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ እንድታደርግ ማን ፈቀደልህ? እስኪ ንገረን” አሉት። 3እርሱም መልሶ፥ “እኔም አንዲት ነገርን እጠይቃችኋለሁ፤ ንገሩኝ፤ 4የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ናት? ከሰማይ ናትን? ወይስ ከሰው?” አላቸው። 5እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፤ “ከሰማይ ነው ብንለው ለምን አላመናችሁትም? ይለናል። 6ከሰው ነው ብንለውም ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ሁሉም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ሆነ አምነውበታልና። 7ከወዴት እንደ ሆነች አናውቅም” ብለው መለሱለት። 8ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔም ይህን በማን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
ስለ ወይን ጠባቂዎች
9 #
ኢሳ. 5፥1። ለሕዝቡም ይህን ምሳሌ ይመስልላቸው ጀመረ፤ እንዲህም አላቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭመቂያም አስቈፈረ፤ ግንብም ሠራለት፤#“መጭመቂያም አስቈፈረ ግንብም ሠ ራለት” የሚለው በግሪኩ የለም። ለገባሮችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይመለስም ዘገየ። 10የመከሩ ወራት በሆነ ጊዜም ወደ ገባሮቹ፥ ከወይኑ ፍሬ ይልኩለት ዘንድ አገልጋዩን ላከ፤ ገባሮቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን ሰደዱት። 11ዳግመኛም ሌላውን አገልጋዩን ላከ፤ እርሱንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን ሰደዱት። 12ደግሞ ሦስተኛውን አገልጋዩን ላከ፤ እርሱንም አቍስለው ሰደዱት። 13የወይኑ ባለቤትም፦ እንግዲህ ምን ላድርግ? ምናልባት እርሱን እንኳ አይተው ያፍሩ እንደ ሆነ የምወደውን ልጄን ልላክ ብሎ ላከው። 14ገባሮቹም ባዩት ጊዜ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እንውሰድ ብለው ተማከሩ። 15ከወይኑ ቦታም ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። 16የወይኑ ባለቤት በመጣ ጊዜ እንግዲህ ምን ያደርጋቸዋል? ይመጣል፤ እነዚያንም ገባሮች ይገድላቸዋል፤ ወይኑንም ለሌሎች ገባሮች ይሰጣል፤” ቃሉንም ሰምተው፥ “አይሆንም፤ እንዲህ አይደረግም” አሉ። 17#መዝ. 117፥22። ጌታችን ኢየሱስም ተመለከተና እንዲህ አላቸው፤ “ግንበኞች የናቁአት ድንጋይ እርስዋ የማዕዘን ራስ ሆነች፥ የሚለው ጽሑፍ ምንድነው? 18በዚያች ድንጋይ ላይ የወደቀ ሁሉ ይቀጠቀጣል፤ እርስዋም የወደቀችበትን ታደቅቀዋለች።” 19ያን ጊዜም የካህናት አለቆችና ጻፎች ሊይዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነርሱ እንደ መሰለ ዐውቀዋልና፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩአቸው።
ለቄሣር ግብር ስለ መስጠት
20ከእነርሱም ተለይተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚጠባበቁትን አዘጋጁለት፤ በአነጋገሩም ያስቱት ዘንድ ወደ መኳንንትና ወደ መሳፍንት አሳልፈው ሊሰጡት ራሳቸውን የሚያመጻድቁ ሰላዮችን ወደ እርሱ ላኩ። 21እነርሱም እንዲህ ብለው ጠየቁት፥ “መምህር ሆይ፥ አንተ እውነት እንደምትናገርና እንደምታስተምር፥ ፊት አይተህም እንደማታዳላ፥ የእግዚአብሔርንም መንገድ በቀጥታ እንደምታስተምር እናውቃለን። 22ለቄሣር ግብር መስጠት ይገባል? ወይስ አይገባም?” 23ተንኰላቸውንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈትኑኛላችሁ? ገንዘቡን አሳዩኝ” አላቸው። 24አምጥተውም አሳዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕፈቱስ የማነው?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “የቄሣር ነው” ብለው መለሱለት። 25እርሱም፥ “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር፥ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው። 26በሕዝቡም ሁሉ ፊት በአነጋገሩ ማሳሳት ተሳናቸው፤ መልሱንም አድንቀው ዝም አሉ።
ስለ ትንሣኤ ሙታን
27“ሙታን አይነሡም” ከሚሉ ከሰዱቃውያንም አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ። 28#ዘዳ. 25፥5። እነርሱም እንዲህ ብለው ጠየቁት፥ “መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወንድሙ ልጅ ሳይወልድ ሚስቱን ትቶ የሞተበት ሰው ቢኖር ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎልናል። 29እንግዲህ ከእኛ ዘንድ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ ታላቁ ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ። 30እንደዚሁም ሁለተኛው አገባት፤ እርሱም ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ 31ሦስተኛውም አገባት፤ እንዲሁም ሰባቱ ሁሉ አገቡአት፤ ልጅ ሳይወልዱም ሞቱ። 32ከሁሉም በኋላ ያቺ ሴት ሞተች። 33እንግዲህ ሙታን በሚነሡበት ጊዜ ከእነርሱ ለማንኛው ሚስት ትሆናለች? ሰባቱም ሁሉ አግብተዋት ነበርና።” 34ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ፥ ይጋባሉም፤ ይወልዳሉ፥ ይዋለዳሉም።#“... ይወልዳሉ ይዋለዳሉም ...” የሚለው በግሪኩ የለም። 35ያን ዓለምና የሙታንን ትንሣኤ ሊወርሱ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም፤ አይጋቡም። 36እንግዲህ ወዲህ ሞት የለባቸውም፤ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ናቸው እንጂ፤ የትንሣኤ ልጆችም ስለሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ። 37#ዘፀ. 3፥6። ሙታን እንደሚነሡስ እግዚአብሔር፦ ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ’ ብሎ በቍጥቋጦው ዘንድ እንደ አነጋገረው ሙሴ ተናግሮአል። 38እንኪያስ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ ሁሉም በእርሱ ዘንድ ሕያዋን ናቸውና።” 39ከጻፎችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መምህር ሆይ፥ መልካም ብለሃል” ብለው መለሱ። 40ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠይቀው የደፈረ ማንም የለም።
ስለ መሲሕ የቀረበ ጥያቄ
41እንዲህም አላቸው፥ “ክርስቶስን እንዴት የዳዊት ልጅ ይሉታል? 42እርሱ ራሱ ዳዊት በመዝሙር መጽሐፍ ‘ጌታ ጌታዬን በቀኜ ተቀመጥ፥ 43#መዝ. 109፥1። ጠላቶችህን ከእግርህ ጫማ በታች እስከ አደርጋቸው ድረስ’ ብሏል። 44እንግዲህ እርሱ ራሱ ዳዊት ‘ጌታዬ’ ያለው እንዴት ልጁ ይሆናል?”
ደቀ መዛሙርቱን ስለ ማስጠንቀቁ
45ሕዝቡም ሲሰሙ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው። 46“ልብሳቸውን አንዘርፍፈው ወዲያ ወዲህ ማለትን ከሚሹ፥ በገበያ እጅ መነሣትንና በአደባባይ ፊት ለፊት፥ በማዕድም ጊዜ በከበሬታ መቀመጫ መቀመጥን ከሚወዱ ጻፎች ተጠበቁ። 47የመበለቶችን ገንዘብ የሚበሉ፥ ለምክንያት ጸሎትንም የሚያስረዝሙ እነዚህ ታላቅ ፍርድን ይቀበላሉ።”
Právě zvoleno:
የሉቃስ ወንጌል 20: አማ2000
Zvýraznění
Sdílet
Kopírovat
Chceš mít své zvýrazněné verše uložené na všech zařízeních? Zaregistruj se nebo se přihlas