Logo YouVersion
Ikona vyhledávání

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 13

13
ስለ ንስሓ
1በዚያ ወራ​ትም ሰዎች ወደ እርሱ መጥ​ተው ጲላ​ጦስ ደማ​ቸ​ውን ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ጋር ስለ ቀላ​ቀ​ለው ስለ ገሊላ ሰዎች ነገ​ሩት። 2ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህች መከራ ስለ አገ​ኘ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ገሊ​ላ​ው​ያን ከገ​ሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​ኣ​ተ​ኞች የሆኑ ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን? 3አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ። 4ወይስ እነ​ዚያ በሰ​ሊ​ሆም ግንብ ተጭኖ የገ​ደ​ላ​ቸው ዐሥራ ስም​ንቱ ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎች ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​እ​ታ​ኞች ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን? 5አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”
ፍሬ ስለ​ሌ​ላት በለስ
6እን​ዲ​ህም ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው፥ “አንድ ሰው በታ​ወ​ቀች በወ​ይኑ ቦታ ውስጥ#በግ​ሪኩ “የተ​ተ​ከ​ለች” ይላል። በለስ ነበ​ረ​ችው፤ ፍሬ​ዋን ሊወ​ስድ ወደ እር​ስዋ ሄዶ አላ​ገ​ኘም። 7የወ​ይ​ኑን ጠባ​ቂም፦#በግ​ሪኩ “የወ​ይን አት​ክ​ልት ሠራ​ተ​ኛ​ውን” ይላል። “የዚ​ችን በለስ ፍሬ ልወ​ስድ ስመ​ላ​ለስ እነሆ፥ ሦስት ዓመት ነው፤ አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ምድ​ራ​ች​ንን እን​ዳ​ታ​ቦ​ዝን ቍረ​ጣት” አለው። 8እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ አፈር ቈፍሬ በሥሯ እስከ አስ​ታ​ቅ​ፋት፥ ፍግም እስከ አፈ​ስ​ባት ድረስ የዘ​ን​ድ​ሮን እንኳ ተዋት። 9ምና​ል​ባት ለከ​ርሞ ታፈራ እንደ ሆነ፥ ያለ​ዚያ ግን እን​ቈ​ር​ጣ​ታ​ለን።”
በሰ​ን​በት ቀን ስለ ዳነ​ችው ሴት
10በሰ​ን​በ​ትም በአ​ንድ ምኵ​ራብ ውስጥ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው። 11ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሙሉ ጋኔን ያጐ​በ​ጣት አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ ጐባ​ጣም ነበ​ረች፤ ከቶ ቀጥ ብላ መቆም አት​ች​ልም ነበር። 12ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አይቶ ራራ​ላት፥#በግ​ሪኩ “ራራ​ላት” አይ​ልም። ጠር​ቶም፥ “ሴትዮ፥ ከደ​ዌሽ ተፈ​ት​ተ​ሻል” አላት። 13እጁ​ንም በላ​ይዋ ጫነ፤ ያን​ጊ​ዜም ፈጥና ቀጥ አለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነ​ችው። 14#ዘፀ. 20፥9-10፤ ዘዳ. 5፥13-14። የም​ኵ​ራቡ ሹምም ጌታ ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ፈው​ሶ​አ​ልና፤ እየ​ተ​ቈጣ መልሶ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሥራ​ች​ሁን የም​ት​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ስድ​ስት ቀኖች ያሉ አይ​ደ​ለ​ምን? ያን​ጊዜ ኑና ተፈ​ወሱ፤ በሰ​ን​በት ቀን ግን አይ​ሆ​ንም።” 15ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “እና​ንት ግብ​ዞች፥ እና​ን​ተሳ አህ​ያ​ች​ሁን ወይም በሬ​አ​ች​ሁን በሰ​ን​በት ቀን ገለባ ከሚ​በ​ላ​በት አት​ፈ​ቱ​ት​ምን? ውኃ ልታ​ጠ​ጡ​ትስ አት​ወ​ስ​ዱ​ት​ምን? 16ይህቺ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይ​ጣን ከአ​ሰ​ራት ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ነው፤ እር​ስ​ዋስ በሰ​ን​በት ቀን ከእ​ስ​ራቷ ልት​ፈታ አይ​ገ​ባ​ምን?” 17ይህ​ንም ባለ ጊዜ በእ​ርሱ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት የተ​ነ​ሡ​በት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእ​ርሱ ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላ​ቸው።
ስለ ሰና​ፍጭ ቅን​ጣት ምሳሌ
18በዚያ ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መን​ግ​ሥተ ሰማ​ያት#በግ​ሪኩ “መን​ግ​ሥተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። ምን ትመ​ስ​ላ​ለች? በም​ንስ እመ​ስ​ላ​ታ​ለሁ? 19ሰው ወስዶ በእ​ርሻ ውስጥ የዘ​ራት የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣ​ትን ትመ​ስ​ላ​ለች፤ አደ​ገች፤ ታላቅ ዛፍም ሆነች፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ውስጥ ተጠ​ለሉ።”
ስለ እርሾ
20ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት በምን እመ​ስ​ላ​ታ​ለሁ? 21ሴት ወስዳ ሦስት መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት የለ​ወ​ሰ​ች​በ​ትን፥ ሁሉ​ንም እን​ዲ​ቦካ ያደ​ረ​ገ​ውን እርሾ ትመ​ስ​ላ​ለች”።
ስለ​ሚ​ድ​ኑት
22በየ​ከ​ተ​ማ​ውና በየ​መ​ን​ደሩ እየ​ሄደ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እየ​ተ​መ​ላ​ለሰ ያስ​ተ​ምር ነበር። 23አንድ ሰውም፥ “አቤቱ የሚ​ድኑ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውን?” አለው። እርሱ ግን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ 24“ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ግን አይ​ች​ሉም። 25ባለ​ቤቱ ተነ​ሥቶ ደጁን ይዘ​ጋ​ልና፤ ያን​ጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈ​ት​ልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀ​ም​ራሉ፤ መል​ሶም፦ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም ይላ​ቸ​ዋል። 26ከዚ​ህም በኋላ፦ በፊ​ትህ በላን፥ ጠጣን፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ያ​ች​ንም አስ​ተ​ማ​ርህ ልትሉ ትጀ​ም​ራ​ላ​ችሁ። 27#መዝ. 6፥8። እር​ሱም እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ እና​ንተ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም፤ ዐመ​ፅን የም​ታ​ደ​ርጉ ሁላ​ችሁ፥ ከእኔ ራቁ፤ 28#ማቴ. 22፥13፤ 25፥30። አብ​ር​ሃ​ምን፥ ይስ​ሐ​ቅ​ንና ያዕ​ቆ​ብን፥ ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በአ​ያ​ች​ኋ​ቸው ጊዜ እና​ን​ተን ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ልቅ​ሶና ጥርስ ማፋ​ጨት ይሆ​ናል። 29#ማቴ. 8፥11-12። ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከሰ​ሜ​ንና ከደ​ቡብ ይመ​ጣሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት በማ​ዕድ ይቀ​መ​ጣሉ፤ 30#ማቴ. 19፥30፤ 20፥16፤ ማር. 10፥31። ኋለ​ኞች ፊተ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ ፊተ​ኞ​ችም ኋለ​ኞች ይሆ​ናሉ።”
ስለ ሄሮ​ድስ
31በዚ​ያ​ችም ቀን ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን ሰዎች መጥ​ተው፥ “ከዚህ ውጣና ሂድ፤ ሄሮ​ድስ ሊገ​ድ​ልህ ይሻ​ልና” አሉት። 32እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱና ያችን ቀበሮ እን​ዲህ በሉ​አት፤ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋ​ን​ን​ትን አወ​ጣ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ት​ንም አድ​ላ​ለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን እፈ​ጽ​ማ​ለሁ። 33ዛሬና ነገስ አለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ግን እሄ​ዳ​ለሁ፤#በግ​ሪኩ “ዛሬና ነገ ከነገ ወዲ​ያም እሄ​ዳ​ለሁ” ይላል። ነቢይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንጂ በውጭ ሊሞት አይ​ገ​ባ​ው​ምና።
ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መፈ​ታት
34“ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ። 35#መዝ. 117፥26፤ ኤር. 22፥5። እነሆ፥ ቤታ​ችሁ ምድረ በዳ ሆኖ ይቀ​ር​ላ​ች​ኋል፤ ከዛሬ ወዲያ ‘በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው’ እስ​ክ​ትሉ ድረስ እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።”

Zvýraznění

Sdílet

Kopírovat

None

Chceš mít své zvýrazněné verše uložené na všech zařízeních? Zaregistruj se nebo se přihlas

Video k የሉ​ቃስ ወን​ጌል 13