ኦሪት ዘፍጥረት 43
43
1ራብም በምድር ጸና። 2ከግብፅም ያመጡትን እህል በልተው ከፈጸሙ በኍላ አባታቸው፦ እንደ ገና ሂዱ ጥቂት እህል ሸምቱልን አላቸው። 3ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዪም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን። 4ወንድማችንን ከእና ጋር ብትሰድደው እንወርዳለን እህልም እንሸምትልሃለን ባትሰድደው ግን አንሄድም፤ 5ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዮም ብሎናልና። 6እስራኤልም አላቸው ለምን በደላችሁኝ? ለዚያውስ፦ ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁን? 7እነርሱም አሉ፦ ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ወገናችን ፈጽሞ ጠየቀን እንዲህም አለን፦ አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን? እኛም እንደዚሁ እንደ ጥያቄው መለስንለት በውኑ፦ ወንድማችሁን አምጡ እንዲለን እናውቅ ነበርነን? 8ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው፦ እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ስደደው እናም ተንሥተን እንሄዳለን። 9እኔ ስለ እርሱ እዋሳለሁ ከእጄ ትሻዋለህ ወደ አንተ ባላመጣው በፊትህም ባላቆመው በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁ ልሁን። 10ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር። 11እስራኤልም አባታቸው እንዲህ አላቸው፦ ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህንን አድርጉ ከተመሰገነው ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ ጥቂት በለሳን ጥቂት ማር ሽቱ፥ ከርቤ፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ። 12ብሩን በአጠፌታ አድርጋችሁ በእጃችሁ ውሰዱ በዓይበታችሁ አፍ የተመለሰውንም ብር መልሳችሁ ውሰዱ ምናልባት በስሕተት ይሆናል። 13ወንድማችሁንም ውሰዱ ተነሥታችሁም ወደዚያ ሰው ተመለሱ። 14ሁሉን የሚችል አምላክም ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ከእናንተ ጋር ይሰድድ ዘንድ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይስጣችሁ እኔም ልጆቼን እንዳጣሁአጣሁ። 15ሰዎቹም በእጅቸው ያችን እጅ መንሻና አጠፌታውን ብር ብንያምንም ወሰዱ ተነሥተውም ወደ ግብፅ ወረዱ፥ በዮሴፍም ፊት ቆሙ።
16ዮሴፍን ብንያምብ ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ እነዚይን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው እርስም እረድ አዘጋጅም፥ እነዚይ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና። 17ያ ስውም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ ያ ሰውም ስዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባ። 18እነርሱም ወደ ዮሴፍ ቤት ስለ ገቡ ፈሩ እንዲህም አሉ፦ በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኮልብን ሊወድቅብንም እኛንም በባርነት ሊገዛ አህዮቻችንንም ሊወስድ ወደዚህ አስገባን። 19ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ፥ ቀረቡ በቤቱ ደጅ ተናገሩት እንዲህም አሉት፦ 20ጌታዬም ሆይ ቀድሞ እህልን ልንሸምት ወርደን ነበር 21ወደምናድርበትም ስፍራ በደረስን ጊዜ ዓይበታችንን ከፈርን እነሆም የእያንዳንዱ ሰው ብር በየዓይበቱ አፍ እንደ ሚዛኑ ብራችን ነበረ፤ አሁንም በእጃችን መለስነው። 22እህል እንሽምትበር ዘንድ ሌላም ብር በእጃችን አመጣን ብራችንንም በዓይበታችን ማን እንደ ጨመረው አናውቅም። 23እርሱም አላቸው፦ ስላም ለእናንተ ይሁን አትፍሩ አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ ብራችሁስ ደርሶኛል። 24ስምዖንም አወጣላቸው። ሰውዮውም እነዚያን ስዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው ውኃ አመጣላቸው እግራቸውንም ታጠቡ ለአህዮቻቸው አበቅ ስጣቸው። 25ዮሴፍም በእኩለ ቀን እስኪገባ ድረስ እነርሱ እጅ መንሻቸው አዘጋጁ ከዚያ እንጀራን እንደሚበሉ ሰምተዋልና። 26ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለው እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት። 27እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው እንዲህም አለ፦ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን? 28እነርሱ አሉት፦ ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው ገና በሕወይት አለ፤ አጎንብሰውም ሰገዱለት። 29ዓይኑንም አንሥቶ የእናቱን ልጅ ብንያምን አያው እርሱም አለ፦ የነገራችህኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን? እንዲህም አለው፦ ልጄ ሆይ እግዚአብሔር ይባርክህ። 30ዮሴፍም ቸኮለ፥ አንጀቱ ወንድሙን ናፍቆታልና ሊያለቅስም ወደደ ወደ እልፍኙም ገብቶ ከዚያ አለቀሰ። 31ፊቱንም ታጥቦ ወጣ ልቡንም አስታግሦ፦ እንጀራ አቅርቡ አለ። 32ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ ለእነርሱም ለብቻቸው ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና። 33በፊቱም በኵሩ እንደ ታላቅነቱ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ ተቀመጡ ሰዎቹም እርስ በርሳቸው ተደነቁ። 34በፊቱም ካለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው የብንያም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ እነርሱም ጠጡ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 43: አማ54
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in