መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 3
3
1ሌሊት በምንጣፌ ላይ
ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፤
ፈለግሁት አላገኘሁትም።
ጠራሁት አልመለሰልኝም።
2እነሣለሁ በከተማዪቱም እዞራለሁ፥
ነፍሴ የወደደችውን
በገበያና በአደባባይ እፈልጋለሁ፤
ፈለግሁት አላገኘሁትም።
ጠራሁት አልመለሰልኝም። #በግእዝ ብቻ።
3ከተማዪቱን የሚጠብቁት ጠባቂዎች አገኙኝ፤
ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸው።
4ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ
ያንጊዜ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም፤
ወደ እናቴም ቤት፥ ወደ ወላጅ እናቴም እልፍኝ
እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
5እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥
ወድዶ እስኪነሣ
ፍቅሬን እንዳትቀሰቅሱትና እንዳታስነሡት፥
በምድረ በዳው ኀይልና ጽንዐት አምላችኋለሁ።
6መዓዛዋ እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነው፥
ከልዩ የሽቱ ቅመም ሁሉ የሆነው፥
ይህች ከምድረ በዳ እንደ ጢስ ዐምድ የወጣችው ማን ናት?
7እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፤
ከእስራኤል ኀያላን ስድሳ ኀያላን በዙሪያዋ ናቸው።
8ሁሉም ሰይፍ የያዙና ሰልፍ የተማሩ ናቸው፤
በሌሊት ከሚወድቀው ፍርሀት የተነሣ
ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።
9ንጉሡ ሰሎሞን መሸከሚያን
ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።
10ምሰሶዎቹን የብር አደረገ፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥
መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፤
ውስጡ ሰንፔር በሚባል ዕንቍ የተለበጠ ነው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በኢየሩሳሌም ልጆች ፍቅር የተለበጠ ነው” ይላል።
ከኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ይልቅ እወድደዋለሁ።
11እናንት የጽዮን ቈነጃጅት፥
እናቱ በሠርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን
ያቀዳጀችውን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን ታዩ ዘንድ ውጡ።
Currently Selected:
መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 3: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in