YouVersion Logo
Search Icon

መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 2

2
1እኔ የዱር ጽጌ​ረዳ፥ የቈ​ላም የሱፍ አበባ ነኝ።
2በእ​ሾህ መካ​ከል እን​ዳለ የሱፍ አበባ፥
እን​ዲሁ ወዳጄ በቈ​ነ​ጃ​ጅት መካ​ከል ነሽ።
3በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥
እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በል​ጆች” ይላል። መካ​ከል ነው።
ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥
ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።
4ወደ ወይን ቤት አገ​ቡኝ፥
በእ​ኔም ላይ ፍቅ​ርን አደ​ረጉ።
5በሽቱ አጸ​ኑኝ፥#ዕብ. “በዘ​ቢብ አጸ​ኑኝ” ይላል።
በእ​ን​ኮ​ይም አበ​ረ​ታ​ቱኝ፥
በፍ​ቅሩ ተነ​ድ​ፌ​አ​ለ​ሁና።
6ቀኙ ታቅ​ፈ​ኛ​ለች።
ግራ​ውም ከራሴ በታች ናት፥
7እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥
ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ፥
ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥
በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽናት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።
8እነሆ፥ የልጅ ወን​ድሜ ቃል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የወ​ን​ድሜ ቃል” ይላል። በተ​ራ​ሮች ላይ ሲዘ​ልል፥
በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሲወ​ረ​ወር ይመ​ጣል።
9ልጅ ወን​ድሜ በቤ​ቴል ተራ​ሮች ላይ ሚዳ​ቋን ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ም​ቦሳ ይመ​ስ​ላል፤
እነሆ፥ በመ​ስ​ኮ​ቶች ሲጐ​በኝ፥
በዐ​ይነ ርግ​ብም ሲመ​ለ​ከት፥
እርሱ ከቅ​ጥ​ራ​ችን በኋላ ቆሞ​አል።
10ልጅ ወን​ድሜ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ልኝ፦
ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥
መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ።
11እነሆ፥ ክረ​ምቱ ዐለፈ፥
ዝና​ሙም አልፎ ሄደ፤
12አበባ በም​ድር ላይ ታየ፥
የመ​ከ​ርም ጊዜ ደረሰ፥#ዕብ. “የዜማ ጊዜ ደረሰ” ይላል።
የቍ​ር​ዬ​ውም ቃል በም​ድ​ራ​ችን ተሰማ።
13በለሱ ጐመራ፥ ወይ​ኖ​ችም አበቡ፥
መዓ​ዛ​ቸ​ው​ንም ሰጡ፤
ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤
መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ።
በዐ​ለት ንቃ​ቃ​ትና በገ​ደል መሸ​ሸ​ጊያ ወዳ​ለው ጥላ ነዪ።
14ፊት​ህን አሳ​የኝ፥
ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤#ዕብ. “ፊት​ሽን አሳ​ይኝ ቃል​ሽ​ንም አሰ​ሚኝ ቃልሽ ያማረ ፊት​ሽም የተ​ዋበ ነውና” ይላል።
ቃልህ ያማረ፥
ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።
15የወ​ይን ቦታ​ችን ያብብ ዘንድ፥
የወ​ይ​ና​ች​ንን ቦታ የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን
ጥቃ​ቅ​ኑን ቀበ​ሮች አጥ​ም​ዳ​ችሁ ያዙ​ልን።
16ልጅ ወን​ድሜ የእኔ ነው፥ እኔም የእ​ርሱ ነኝ፤
በሱፍ አበ​ባ​ዎች መካ​ከ​ልም መን​ጋ​ውን ያሰ​ማ​ራል።
17ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስ​ኪ​ነ​ፍስ፥
ጥላ​ውም እስ​ኪ​ሸሽ ድረስ ተመ​ለስ፤
በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋ​ውን
ወይም የዋ​ላ​ውን እን​ቦሳ ምሰል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in