YouVersion Logo
Search Icon

መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 1

1
1ከመ​ዝ​ሙር ሁሉ የሚ​በ​ልጥ የሰ​ሎ​ሞን መዝ​ሙር።
2በአፉ አሳ​ሳም ይስ​መ​ኛል፥
ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ ያማሩ ናቸው።#በዕብ. ከቍ. 2 እስከ 7 መጨ​ረሻ መር​ዓት ለመ​ር​ዓዊ ትና​ገ​ራ​ለች።
3የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥
ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤
ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።
4ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤
ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤
በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤
ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤
አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።
5እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤
ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።
6ፀሓይ መል​ኬን አክ​ስ​ሎ​ታ​ልና
ጥቁር ስለ ሆንሁ አት​ዩኝ፤
የእ​ናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥
የወ​ይን ቦታ​ዎ​ች​ንም ጠባቂ አደ​ረ​ጉኝ፤
ነገር ግን የእ​ኔን የወ​ይን ቦታ አል​ጠ​በ​ቅ​ሁም።
7ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ችህ አንተ ንገ​ረኝ፤
በባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ችህ መን​ጎች መካ​ከል የተ​ቅ​በ​ዘ​በ​ዝሁ እን​ዳ​ል​ሆን፥
ወዴት ታሰ​ማ​ራ​ለህ? በቀ​ት​ርስ ጊዜ ወዴት ትመ​ሰ​ጋ​ለህ?
8አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥
ያላ​ወ​ቅሽ እንደ ሆነ የመ​ን​ጎ​ችን ፍለጋ ተከ​ት​ለሽ ውጪ፥
የፍ​የል ግል​ገ​ሎ​ች​ሽ​ንም በእ​ረ​ኞች ድን​ኳ​ኖች አጠ​ገብ አሰ​ማሪ።
9ወዳጄ ሆይ፥ በፈ​ር​ዖን ሰረ​ገ​ሎች እን​ዳለ ፈረሴ መሰ​ል​ሁሽ።
10ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥
አን​ገ​ት​ሽም በዕ​ንቍ ድሪ ያማረ ነው።
11ባለ ብር ጕብ​ጕብ የሆነ የወ​ርቅ ጠል​ሰም ያድ​ር​ጉ​ልሽ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እና​ደ​ር​ግ​ል​ሻ​ለን” ይላል።
12ንጉሡ በማ​ዕድ እስ​ከ​ሚ​ቀ​ርብ ድረስ፥
የእኔ ናር​ዶስ መዓ​ዛ​ውን ሰጠ።
13ውዴ ለእኔ በጡ​ቶች መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ያ​ርፍ
እንደ ተቋ​ጠረ ከርቤ ነው።
14ልጅ ወን​ድሜ ለእኔ በዐ​ይ​ን​ጋዲ ወይን ቦታ እን​ዳለ
እንደ አበባ ዕቅፍ ነው።
15ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤
እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤
ዐይ​ኖ​ች​ሽም እንደ ርግ​ቦች ናቸው።
16ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥
መልከ መል​ካ​ምም ነህ፤
አል​ጋ​ች​ንም ለም​ለም ነው።
17የቤ​ታ​ችን ሰረ​ገላ የዝ​ግባ ዛፍ ነው፥
የጣ​ሪ​ያ​ች​ንም ማዋ​ቀ​ሪያ የጥድ ዛፍ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in