መዝሙረ ዳዊት 99
99
የምስጋና መዝሙር።
1በምድር ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥
2በደስታም ለእግዚአብሔር ተገዙ፥
በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ።
3እግዚአብሔር እርሱ አምላካችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤
እርሱ ፈጠረን፥ እኛም አይደለንም፤
እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያውም በጎች ነን።
4ወደ ደጆቹ በመገዛት፥
ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤
አመስግኑት፥ ስሙንም አክብሩ፥
5እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም፥
እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 99: አማ2000
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in