መዝሙረ ዳዊት 81
81
የአሳፍ መዝሙር።
1እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥
በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
2እስከ መቼ ዐመፃን ትፈርዳላችሁ?
እስከ መቼስ ለኀጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?
3ለድሆችና ለድሃ አደጎች ፍረዱ፤
ለተገፋውና ለምስኪኑ ጽድቅን አድርጉ፤
4ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤
ከኃጥኣንም እጅ አስጥሉአቸው።
5አያውቁም፥ አያስተውሉምም፤
በጨለማ ውስጥም ይመላለሳሉ፤
የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6እኔ ግን እላለሁ፥ “አማልክት ናችሁ፥
ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤”
7እናንተ ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥
ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
8አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥
አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 81: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in