YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 81

81
የአ​ሳፍ መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ማ​ል​ክት ማኅ​በር ቆመ፥
በአ​ማ​ል​ክ​ትም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል።
2እስከ መቼ ዐመ​ፃን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ?
እስከ መቼስ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ፊት ታደ​ላ​ላ​ችሁ?
3ለድ​ሆ​ችና ለድሃ አደ​ጎች ፍረዱ፤
ለተ​ገ​ፋ​ውና ለም​ስ​ኪኑ ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤
4ብቸ​ኛ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን አድኑ፤
ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ አስ​ጥ​ሉ​አ​ቸው።
5አያ​ው​ቁም፥ አያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤
በጨ​ለማ ውስ​ጥም ይመ​ላ​ለ​ሳሉ፤
የም​ድር መሠ​ረ​ቶች ሁሉ ተና​ወጡ።
6እኔ ግን እላ​ለሁ፥ “አማ​ል​ክት ናችሁ፥
ሁላ​ች​ሁም የል​ዑል ልጆች ናችሁ፤”
7እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥
ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።
8አቤቱ፥ ተነሥ፥ በም​ድር ላይ ፍረድ፥
አንተ አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ትወ​ር​ሳ​ለ​ህና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in