መዝሙረ ዳዊት 76
76
ለመዘምራን አለቃ ስለ ኤዶታም የአሳፍ መዝሙር።
1በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥
ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።
2በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤
እጆቼም በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ ጠላቶቼም አልረገጡኝም።
ነፍሴ ግን ደስታን አጣች።#ዕብ. “መጽናናትን አልቻለችም” ይላል።
3እግዚአብሔርን ዐሰብሁት፥ ደስ አለኝም፤
ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች።
የጠላቶቼን ሁሉ ሰዓቶች ዐወቅኋቸው#ዕብ. “ዐይኖች እንዲተጉ ጠበቅሃቸው” የሚል ይጨምራል።
4ደነገጥሁ አልተናገርሁምም።
5የድሮውን ዘመን ዐሰብሁ፤
የዘለዓለሙን ዓመታት ዐሰብሁ፤ አነበብኹም፤
6በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥
መንፈሴንም አነቃቃኋት።
7እግዚአብሔር ለዘለዓለም በውኑ ይጥላልን?
እንግዲህስ ይቅርታውን አይጨምርምን?
8ለዘለዓለምስ ምሕረቱን ለልጅ ልጅ ይቈርጣልን?
9እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን?#ዕብ. ይጨምራል።
በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን?
10እነሆ፥ ዛሬ ጀመርሁ አልሁ፥
ልዑል ቀኙን እንደሚያፈራርቅ።
11የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ፤
የቀደመውን ተአምራትህን አስታውሳለሁና፤
12በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥
በሥራህም እጫወታለሁ።
13አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፤
እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
14ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤
ለሕዝብህ ኀይልህን አሳየሃቸው።
15የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥
ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው።
16አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥
ውኆች አይተው ፈሩ፤
የውኆች ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆቻቸውም ጮኹ።
17ደመናት ድምፅን ሰጡ፥
ፍላጾችህም ወጡ።
18የነጐድጓድህ ድምፅ በሰረገላ#ዕብ. “በዐውሎ” ይላል። ነበረ፤
መብረቆች ለዓለም አበሩ፤
ምድር ተናወጠች፥ ተንቀጠቀጠችም።
19መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥
ፍለጋህም በብዙ ውኆች ነው፥
ፍለጋህም አይታወቅም።
20በሙሴና በአሮን እጅ
ሕዝብህን እንደ በጎች መራሃቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 76: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in