YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 75

75
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በበ​ገ​ና​ዎች ስለ አሦ​ራ​ው​ያን የአ​ሳፍ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ታወቀ፥
ስሙም በእ​ስ​ራ​ኤል ታላቅ ሆነ።
2በሀ​ገ​ሩም በሰ​ላም ኖረ፥#ዕብ. “ድን​ኳኑ በሳ​ሌም ነው” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቦታው በሰ​ላም ነበር” ይላል። ማደ​ሪ​ያ​ውም በጽ​ዮን ነው፤
3በዚ​ያም የቀ​ስ​ትን ኀይል፥
ጋሻን፥ ጦር​ንና ሰል​ፍ​ንም ሰበረ፤
በዚ​ያም ቀን​ዶ​ችን ሰበረ።
4አንተ በዘ​ለ​ዓ​ለም ተራ​ሮች ሆነህ በድ​ንቅ ታበ​ራ​ለህ።
5ልበ ሰነ​ፎች ሁሉ ደነ​ገጡ፥
ሕል​ምን አለሙ፥ ያገ​ኙት ግን የለም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አን​ቀ​ላፉ በእ​ጃ​ቸው ያገ​ኙት የለም” ይላል።
ሰው ሁሉ ለእጁ ባለ​ጠ​ግ​ነት ነው።
6የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ሆይ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ የተ​ነሣ
ፈረ​ሰ​ኞች ሁሉ አን​ቀ​ላፉ።
7አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤
ቍጣ​ህን ማን ይቃ​ወ​ማል?
8ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ።
ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥
9ልበ የዋ​ሃ​ንን ሁሉ ያድን ዘንድ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለፍ​ርድ በተ​ነሣ ጊዜ።
10ሰው በፈ​ቃዱ ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልና፥
ከሕ​ሊ​ና​ቸው ትር​ፍም በዓ​ል​ህን ያደ​ር​ጋሉ።
11ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለ​ትን ሰጡ፤
በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ ሁሉ እጅ መን​ሻን ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ራው ያገ​ባሉ።
12የአ​ለ​ቆ​ችን ነፍስ ያወ​ጣል፤
በም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ዘንድ ያስ​ፈ​ራል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝ​ሙረ ዳዊት 75