YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 67

67
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይነሣ፥ ጠላ​ቶ​ቹም ይበ​ተኑ፥
የሚ​ጠ​ሉ​ትም ከፊቱ ይሽሹ።
2ጢስ እን​ደ​ሚ​በ​ንን እን​ዲሁ ይብ​ነኑ፤
ሰም በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥
እን​ዲሁ ኃጥ​ኣን ከአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጥፉ።
3ጻድ​ቃን ግን ደስ ይበ​ላ​ቸው፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሐሤ​ትን ያድ​ርጉ፥
በደ​ስ​ታም ደስ ይበ​ላ​ቸው።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ለስ​ሙም ዘምሩ፤
ወደ ምዕ​ራብ ለወ​ጣው መን​ገ​ድን አብጁ፤
ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በፊ​ቱም ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤
ከፊ​ቱም የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱስ ቦታው
ለድሃ አደ​ጎች አባት፥ ለባ​ል​ቴ​ቶ​ችም ዳኛ ነው።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቸ​ኞ​ችን በቤቱ ያሳ​ድ​ራ​ቸ​ዋል፥
እስ​ረ​ኞ​ች​ንም በኀ​ይሉ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል፤
በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ ኀዘ​ን​ተ​ኞ​ች​ንም#ዕብ. “ዐመ​ፀ​ኞች” ይላል። እን​ዲሁ።
7አቤቱ፥ በሕ​ዝ​ብህ ፊት በወ​ጣህ ጊዜ፥
በም​ድረ በዳም ባለ​ፍህ ጊዜ፥
8ከሲና አም​ላክ ፊት፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት
ምድር ተና​ወ​ጠች፥
ሰማ​ያ​ትም አን​ጠ​ባ​ጠቡ።
9አቤቱ፥ በፈ​ቃ​ድህ ዝና​ብን ለር​ስ​ትህ ለየህ፥
በደ​ከ​መም ጊዜ አንተ ታጸ​ና​ዋ​ለህ።
10እን​ስ​ሶ​ችህ በው​ስጡ ያድ​ራሉ፤
አቤቱ፥ በቸ​ር​ነ​ትህ ለድ​ሆች አዘ​ጋ​ጀህ።
11ብዙ ኀይ​ልን ለሚ​ያ​ወሩ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሉን ሰጠ፤
12ለኀ​ያ​ላን ንጉሥ ለወ​ዳጁ፤
ለወ​ዳ​ጁና ለቤ​ትህ ውበት#ዕብ. “የሠ​ራ​ዊት ነገ​ሥ​ታት ፈጥ​ነው ይሸ​ሻሉ በቤ​ትም የም​ት​ኖር” ይላል። ምር​ኮን ተካ​ፈ​ልን።
13በር​ስ​ቶች መካ​ከል ብታ​ድሩ፥
ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክን​ፎች፥
በቅ​ጠ​ልያ ወር​ቅም እንደ ተለ​በጡ ላባ​ዎ​ችዋ ትሆ​ና​ላ​ችሁ።
14ሰማ​ያዊ ንጉሥ በላ​ይዋ ባዘዘ ጊዜ፥#ዕብ. “ሁሉን ቻይ ሰማ​ያዊ በላ​ይዋ ነገ​ሥ​ታ​ትን በበ​ተነ ጊዜ” ይላል።
በሰ​ል​ሞን ላይ በረዶ ይዘ​ን​ማል።
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ የለ​መ​ለመ ተራራ ነው፤
የጸና ተራ​ራና የለ​መ​ለመ ተራራ ነው።
16የጸኑ ተራ​ራ​ዎች ለምን ይነ​ሣሉ?
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ር​በት ዘንድ የወ​ደ​ደው ተራራ ይህ ነው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያድ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ልና።#ዕብ. “ያድ​ር​ባ​ታል” ይላል።
17የብዙ ብዙ ሺህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ዎች ደስ​ተ​ኞች ናቸው።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ በሲና በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነው።
18ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ
ስጦ​ታ​ህ​ንም ለሰ​ዎች ሰጠህ፥ ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበ​ርና።#ዕብ. “ዳግ​ምም ለዐ​መ​ፀ​ኞች በዚያ ያድሩ ዘንድ” ይላል።
19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቡሩክ ነው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በየ​ዕ​ለቱ ቡሩክ ነው፤
አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ይረ​ዳ​ናል።
20አም​ላ​ካ​ች​ንስ የማ​ዳን አም​ላክ ነው፤
የሞት መን​ገድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሞት መው​ጣት ከጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው” ይላል።
21ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጠ​ላ​ቶ​ቹን ራስ ይሰ​ብ​ራል፥
በጠ​ጉ​ራ​ቸው ጫፍም በደ​ላ​ቸው ይሄ​ዳል።
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፦ ወጥቼ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከባ​ሳን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” ይላል።
በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፥
23እግ​ሮ​ችህ በደም ይነ​ከሩ ዘንድ፥
የው​ሾ​ችህ ምላስ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ላይ ነው።
24አቤቱ፥ መን​ገ​ድህ ተገ​ለጠ።
የአ​ም​ላ​ካ​ችን የን​ጉሡ መን​ገድ በመ​ቅ​ደሱ
25አለ​ቆች ደረሱ፥ መዘ​ም​ራ​ንም አሏ​ቸው
ከበ​ሮን በሚ​መቱ በደ​ና​ግል መካ​ከል።
26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጉ​ባኤ፥
አም​ላ​ካ​ች​ን​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ምን​ጮች አመ​ሰ​ገ​ኑት።
27ወጣቱ ብን​ያም በጉ​ል​በቱ በዚያ አለ፥
ገዦ​ቻ​ቸው የይ​ሁዳ አለ​ቆች፥
የዛ​ብ​ሎን አለ​ቆ​ችና የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም አለ​ቆች።
28አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ እዘዝ፤
አቤቱ፥ ይህን ለእኛ የሠ​ራ​ኸ​ውን አጽ​ናው።
29በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው መቅ​ደ​ስህ
ነገ​ሥ​ታት እጅ መን​ሻን ለአ​ንተ ያመ​ጣሉ።
30በቀ​ር​ካሃ ውስጥ ያሉ​ትን አራ​ዊት፥
በሕ​ዝብ ጊደ​ሮች መካ​ከል የበ​ሬ​ዎ​ችን ጉባኤ ገሥጽ፥
እንደ ብር የተ​ፈ​ተ​ኑት አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ዘጉ፤
ሰል​ፍን የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን አሕ​ዛ​ብን በት​ና​ቸው።
31መል​እ​ክ​ተ​ኞች ከግ​ብፅ ይምጡ፤
ኢት​ዮ​ጵያ እጆ​ች​ዋን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትዘ​ረ​ጋ​ለች።
32የም​ድር ነገ​ሥ​ታት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፥
ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ዘምሩ።
33በም​ሥ​ራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማ​ያት ለወጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፤
የኀ​ይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰ​ጣል።
34ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናን ስጡ፤
ግር​ማው በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ፥
ኀይ​ሉም እስከ ደመ​ናት ነው።
35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱ​ሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤
የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እርሱ ኀይ​ልን ብር​ታ​ት​ንም ለሕ​ዝቡ ይሰ​ጣል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 67