YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 66

66
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በበ​ገ​ና​ዎች የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ረን ይባ​ር​ከ​ንም፥
ፊቱ​ንም በላ​ያ​ችን ያብራ፤ እኛም በሕ​ይ​ወት እን​ኑር
2መን​ገ​ድ​ህን በም​ድር፥
በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ ማዳ​ን​ህን እና​ውቅ ዘንድ፥
3አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥
አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።
አሕ​ዛብ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ሐሤ​ትም ያደ​ር​ጋሉ።
4ለአ​ሕ​ዛብ በቅን ትፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥
አሕ​ዛ​ብ​ንም በም​ድር ላይ ትመ​ራ​ለ​ህና
5አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።
አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።
6ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥
የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ከ​ናል፥
የም​ድ​ርም ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 66