YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 59

59
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የሶ​ር​ያን ሁለ​ቱን ወን​ዞ​ችና የሶ​ር​ያን ሶባ​ልን ባቃ​ጠለ ጊዜ ኢዮ​አ​ብም ተመ​ልሶ ከኤ​ዶ​ማ​ው​ያን ሰዎች በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን በገ​ደለ ጊዜ ለት​ም​ህ​ርት የዳ​ዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ ጣል​ኸን አፈ​ረ​ስ​ኸ​ንም፤
ገረ​ፍ​ኸን፥ ይቅ​ርም አል​ኸን።
2ምድ​ርን አና​ወ​ጥ​ሃት፥ አወ​ክ​ሃ​ትም፤
ተና​ው​ጣ​ለ​ችና ቍስ​ል​ዋን ፈወ​ስ​ኻት።#ዕብ. “ፈውስ” ይላል።
3ለሕ​ዝ​ብህ ጭን​ቅን አሳ​የ​ሃ​ቸው፥
አስ​ደ​ን​ጋ​ጩ​ንም ወይን አጠ​ጣ​ኸን።
4ለሚ​ፈ​ሩህ ምል​ክ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው፥
ከቀ​ስት ፊት ያመ​ልጡ ዘንድ።
5ወዳ​ጆ​ች​ህም፥ እን​ዲ​ድኑ
በቀ​ኝህ አድን፥ ስማ​ኝም።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፤
ደስ ይለ​ኛል፥ ምር​ኮ​ንም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሴኬ​ም​ንም” ይላል። እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥
የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።
7ገለ​ዓድ የእኔ ነው፥ ምና​ሴም የእኔ ነው፤
ኤፍ​ሬም የራሴ መጠ​ጊያ ነው።
ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
8ካህን ሞአ​ብም ተስ​ፋዬ ነው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሞአብ የተ​ስ​ፋዬ አፍ​ላል ነው” ሲል ዕብ. “ሞአብ መታ​ጠ​ቢ​ያዬ ነው” ይላል።
በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ ጫማ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤
ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ምም ይገ​ዙ​ል​ኛል።
9ቅጥር ወደ አለ​ባት ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወ​ስ​ደ​ኛል?
ማንስ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ይመ​ራ​ኛል?
10አቤቱ፥ የጣ​ል​ኸን አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?
አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።
11በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፥
በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።
12በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤
እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 59