YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 58

58
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ አታ​ጥፋ። ሳኦል ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ቤቱን እን​ዲ​ጠ​ብቁ በላከ ጊዜ የዳ​ዊት ቅኔ።
1አም​ላኬ ሆይ፥ ከጠ​ላ​ቶች አድ​ነኝ፤
በላ​ዬም ከቆ​ሙት አስ​ጥ​ለኝ።
2ከዐ​መፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ታደ​ገኝ፥
ከደም ሰዎ​ችም አድ​ነኝ።
3እነሆ፥ ነፍ​ሴን አድ​ድ​ነ​ዋ​ታ​ልና፥
ብር​ቱ​ዎ​ችም በላዬ ተነሡ፤
አቤቱ፥ በበ​ደ​ሌም አይ​ደ​ለም፥ በኀ​ጢ​አ​ቴም አይ​ደ​ለም።
4ያለ በደል ሮጥሁ ተዘ​ጋ​ጀ​ሁም፤
ተነሥ፥ ተቀ​በ​ለኝ፥ እይም።
5አን​ተም አቤቱ፥ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አም​ላክ” ይላል።
አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ጐብ​ኛ​ቸው፥ ይቅ​ርም በላ​ቸው፤#ዕብ. “ትጎ​በ​ኛ​ቸው ዘንድ ንቃ” ይላል።
ዐመፅ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ግን አት​ማ​ራ​ቸው።
6ማታ ይመ​ለሱ እንደ ውሾ​ችም ይራቡ፥
በከ​ተ​ማም ይዙሩ።
7እነሆ፥ በአ​ፋ​ቸው ይና​ገ​ራሉ፤
ሰይ​ፍም በከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው አለ፤
8የም​ት​ሰ​ማ​ቸው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ማን ይሰ​ማል” ይላል። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፥
አሕ​ዛ​ቡ​ንም ሁሉ ትን​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥
9ኀይ​ሌን ወደ አንተ አስ​ጠ​ጋ​ለሁ፥
አንተ አም​ላ​ኬና መጠ​ጊ​ያዬ ነህና።
10የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ
አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።
11ሕግ​ህን እን​ዳ​ይ​ረሱ አት​ግ​ደ​ላ​ቸው፤
አቤቱ፥ አም​ላ​ኬና ረዳቴ፥ በኀ​ይ​ልህ በት​ና​ቸው፥ አዋ​ር​ዳ​ቸ​ውም።
12ስለ አፋ​ቸው ኀጢ​አት ስለ ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም ቃል፥ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ይጠ​መዱ
ከመ​ር​ገ​ማ​ቸ​ውና ከሐ​ሰ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ይታ​ወ​ቃል።
13ኋላ በሚ​መጣ መቅ​ሠ​ፍት ያል​ቃሉ፤#ዕብ. “በቍጣ አጥ​ፋ​ቸው እን​ዳ​ይ​ኖ​ሩም አጥ​ፋ​ቸው” ይላል።
የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እን​ዲ​ገዛ ይወቁ።
14ማታ ይመ​ለሱ እንደ ውሾ​ችም ይራቡ፥
በከ​ተ​ማም ይዙሩ።
15እነ​ር​ሱም መብል ለመ​ፈ​ለግ ይበ​ተኑ፤
የጠ​ገቡ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያል​ጠ​ገቡ” ይላል። እንደ ሆነም ያን​ጐ​ራ​ጕ​ራሉ።
16እኔ ግን ለኀ​ይ​ልህ እቀ​ኛ​ለሁ፤
በም​ሕ​ረ​ት​ህም በማ​ለዳ ደስ ይለ​ኛል፤
በመ​ከ​ራዬ ቀን መጠ​ጊ​ያ​ዬና አም​ባዬ ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና።
17አንተ ረዳቴ ነህ፥ ለአ​ን​ተም ለአ​ም​ላኬ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤
አንተ፥ አም​ላኬ፥ መጠ​ጊ​ያዬ ነህና አም​ላ​ኪዬ ምሕ​ረ​ቴም ነህና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 58