መዝሙረ ዳዊት 148
148
የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤
በአርያም ያመሰግኑታል፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. መዝ. 148 ከቍ. 2 እስከ 5 “አመስግኑት” ይላል።
2መላእክቱ ሁሉ ያመሰግኑታል፤
ሠራዊቱ ሁሉ ያመሰግኑታል።
3ፀሐይና ጨረቃ ያመሰግኑታል፤
ከዋክብትና ብርሃን ሁሉ ያመሰግኑታል።
4ሰማየ ሰማያት፥
ከሰማያት በላይ ያለ ውኃም ያመሰግኑታል።
5የእግዚአብሔርንም ስም ያመሰግናሉ።
እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑ፤
እርሱ አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ፤
6ለዘለዓለም አቆማቸው፤
ትእዛዝን ሰጣቸው፥ አላለፉምም።
7እባቦችና ጥልቆች ሁሉ፥
እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት፤
8እሳትና በረዶ፥ አመዳይና ውርጭ፥
ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም፤
9ተራሮችና ኮረብቶችም ሁሉ፥
የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ሁሉ፤
10አራዊትም፥ እንስሳትም ሁሉ፥
ተንቀሳቃሾችም፥ የሚበርሩ ወፎችም፤
11የምድር ነገሥታት፥ አሕዛብም ሁሉ፥
አለቆች፥ የምድርም ፈራጆች ሁሉ፤
12ጐልማሶችና ደናግል፥
ሽማግሌዎችና ልጆች፤
13የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግናሉ።
ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥
በሰማይና በምድር ያመሰግኑታል።
14የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና
ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 148: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in