YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 137

137
የሐ​ጌና የዘ​ካ​ር​ያስ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥
የአ​ፌን ነገር ሁሉ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤
በመ​ላ​እ​ክት ፊት እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።
2በቤተ መቅ​ደ​ስ​ህም እሰ​ግ​ዳ​ለሁ፤
ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ስም​ህን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥
በሁሉ ላይ ቅዱስ ስም​ህን ከፍ ከፍ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና።
3በጠ​ራ​ሁህ ቀን በፍ​ጥ​ነት አድ​ም​ጠኝ፤
ነፍ​ሴን በኀ​ይ​ልህ በብዙ አጸ​ና​ሃት።
4አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤
የአ​ፍ​ህን ቃል ሁሉ ሰም​ተ​ዋ​ልና።
5በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምስ​ጋና ይዘ​ም​ራሉ።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር#ግእዝ “ግብር” ይላል። ታላቅ ነውና።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ያለ ነውና፥
የተ​ዋ​ረ​ዱ​ት​ንም ይመ​ለ​ከ​ታ​ልና፤
ትቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ከሩቁ ያው​ቀ​ዋል።
7በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤
በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን#ግእዝ “እደ​ውየ” ይላል። ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥
ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይበ​ቀ​ል​ል​ኛል፤
አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤
አቤቱ የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል አት​በል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝ​ሙረ ዳዊት 137