መዝሙረ ዳዊት 110
110
ሃሌ ሉያ።
1አቤቱ፥ በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም
በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።
2የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፥
በፈቃዱም ሁሉ የተፈለገች ናት።
3ሥራው ምስጋናና የጌትነት ክብር ነው።
ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4ለጌትነቱ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለተአምራቱ” ይላል። መታሰቢያን አደረገ፤
እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።
5ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤
ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል።
6የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ
ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ።
7የእጆቹ ሥራ እውነትና ቅን ነው፤
ትእዛዙም ሁሉ የታመነ ነው፥
8ለዘለዓለምም የጸና ነው፥
በእውነትና በቅንም የተሠራ ነው።
9እግዚአብሔርም መድኀኒትን ለሕዝቡ ላከ፥
ኪዳኑንም ለዘለዓለም አዘዘ፤
ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው።
10የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥
ለሚያደርጋት ሁሉ ምክር መልካም ናት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለሚያደርጓትም ሁሉ መልካም ማስተዋል አላቸው” ይላል።
ምስጋናውም ለዘለዓለም ይኖራል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 110: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in