YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 2

2
ከት​ዕ​ቢት ስለ መራቅ
1አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ደስታ፥ ወይም በፍ​ቅር የልብ መጽ​ና​ናት፥ ወይም የመ​ን​ፈስ አን​ድ​ነት፥ ወይም ማዘ​ንና መራ​ራ​ትም በእ​ና​ንተ ዘንድ ካለ፦ 2እር​ሱን ብቻ ታስቡ ዘንድ፥ አንድ ልብና አንድ ምክ​ርም ሆና​ችሁ፥ በፍ​ቅር ትኖሩ ዘንድ ደስ​ታ​ዬን ፈጽ​ሙ​ልኝ። 3በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ። 4ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም እንጂ ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ብቻ አታ​ስቡ። 5ፍጹ​ማን የሆ​ና​ችሁ ሁላ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለእኛ እንደ አደ​ረ​ገ​ልን ይህን አስቡ።#ግሪኩ “በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የነ​በረ ይህ አሳብ በእ​ና​ንተ ዘንድ ደግሞ ይኑር” ይላል። 6ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልኩ ነው፤ ቀምቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ አይ​ደ​ለም። 7ነገር ግን የባ​ር​ያን መልክ ይዞ፥ በሰ​ውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደ​ረገ። 8እንደ ሰውም ሆኖ ራሱን አዋ​ረደ፤ ለሞት እስከ መድ​ረ​ስም ታዘዘ፤ ሞቱም በመ​ስ​ቀል የሆ​ነው ነው። 9ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ከስም ሁሉ የሚ​በ​ልጥ ስም​ንም ሰጠው። 10ይህም በሰ​ማ​ይና በም​ድር በቀ​ላ​ያ​ትና#“ቀላ​ያት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ከም​ድር በታች ያለ ጕል​በት ሁሉ ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይሰ​ግድ ዘንድ ነው። 11#ኢሳ. 45፥23። አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው።
12አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ። 13ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።#ግሪኩ “ስለ በጎ ፈቃዱ መፈ​ለ​ግ​ንም፥ ማድ​ረ​ግ​ንም በእ​ና​ንተ የሚ ሠራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና” ይላል። 14የም​ት​ሠ​ሩ​ትን ሁሉ ያለ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ርና ያለ መጠ​ራ​ጠር በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ።#“በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 15#ዘዳ. 32፥5። እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤ 16የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና። 17ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ።#ግሪኩ “በእ​ም​ነ​ታ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕ​ትና አገ​ል​ግ​ሎት ተጨ​ምሬ ሕይ​ወቴ እን​ኳን ቢፈ​ስስ ደስ ይለ​ኛል” ይላል። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ 18እና​ን​ተም በእኔ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ከእ​ኔም ጋር ሐሤት አድ​ርጉ።
ስለ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስና አፍ​ሮ​ዲጡ መላክ
19ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን እን​ድ​ል​ክ​ላ​ችሁ፥ እኔም ዜና​ች​ሁን ሰምቼ ደስ እን​ዲ​ለኝ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 20ከእ​ርሱ በቀር፥ እንደ እኔ ሆኖ በማ​ስ​ተ​ዋል ግዳ​ጃ​ች​ሁን የሚ​ፈ​ጽም የለ​ኝ​ምና። 21የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ያይ​ደለ፥ ሁሉም የራ​ሱን ጉዳይ ያስ​ባ​ልና። 22ልጅ አባ​ቱን እን​ደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግል፥ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት እንደ አገ​ለ​ገ​ለኝ፥ የዚ​ህን ሰው ጠባ​ዩን ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 23እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እንደ አለሁ በዐ​ወ​ቅሁ ጊዜ፥ እር​ሱን በቶሎ እን​ደ​ም​ል​ከው ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ 24እኔም ፈጥኜ እን​ደ​ም​መጣ በጌ​ታ​ችን አም​ና​ለሁ።
25አሁ​ንም አብ​ሮኝ የሚ​ሠ​ራ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን አፍ​ሮ​ዲ​ጡን ወደ እና​ንተ ልል​ከው አስ​ቤ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም የክ​ር​ስ​ቶስ ሎሌ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም መም​ህ​ራ​ችሁ ነው፤ ለእ​ኔም ለች​ግሬ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኛዬ ነው። 26እንደ ታመመ፥ ለሞ​ትም እንደ ደረሰ መስ​ማ​ታ​ች​ሁን ዐውቆ ሊያ​ያ​ችሁ ይሻ​ልና።#ግሪኩ “ሁላ​ች​ሁን ሊያ​ያ​ችሁ ይና​ፍ​ቃ​ልና እንደ ታመ​መም ስለ ሰማ​ችሁ ይተ​ክ​ዛል” ይላል። 27ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማረው፤ በኀ​ዘን ላይ ኀዘን እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ብኝ ለእ​ኔም እንጂ ለእሱ ብቻ አይ​ደ​ለም። 28እን​ድ​ታ​ዩ​ትና ደስ እን​ዲ​ላ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ላ​ዝን በቶሎ እል​ከ​ዋ​ለሁ። 29እን​ግ​ዲህ በጌ​ታ​ችን በፍ​ጹም ደስታ ተቀ​በ​ሉት፤ እን​ደ​ዚህ ያሉ​ት​ንም ሁሉ አክ​ብ​ሩ​አ​ቸው። 30የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ስለ መሥ​ራት እስከ ሞት ደር​ሶ​አ​ልና፥ ከእኔ መል​እ​ክ​ትም እና​ንተ ያጐ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን ይፈ​ጽም ዘንድ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in