YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 1

1
በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ስላሉ ምእ​መ​ናን
1 # የሐዋ. 16፥12። ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ባር​ያ​ዎች ከጳ​ው​ሎ​ስና ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥ በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ለሚ​ኖሩ፤ ከቀ​ሳ​ው​ስ​ትና#ግሪኩ “ከኤ​ጲ​ስ​ቆ​ጶ​ሳ​ትና ...” ይላል። ከዲ​ያ​ቆ​ናት ጋር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፤ 2ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።
የቅ​ዱስ ጳው​ሎስ ጸሎት ለፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች
3እና​ን​ተን በማ​ስ​ብ​በት ጊዜ ሁሉ ዘወ​ትር አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። 4ስለ እና​ን​ተም ሁል​ጊዜ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የደ​ስታ ጸሎ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ። 5ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ከእኔ ጋር አንድ በመ​ሆ​ና​ችሁ፥ 6እርሱ የጀ​መ​ረ​ላ​ች​ሁን በጎ​ውን ሥራ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ እርሱ እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ አም​ና​ለሁ። 7ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና። 8በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ#ግሪኩ “እን​ደ​ም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው። 9ስለ​ዚ​ህም በአ​እ​ም​ሮና በልብ ጥበብ ሁሉ ፍቅ​ራ​ችሁ እን​ዲ​በዛ፥ እን​ዲ​ጨ​ም​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ 10የሚ​ሻ​ለ​ውን ሥራ እን​ድ​ት​መ​ረ​ም​ሩና እን​ድ​ት​ፈ​ትኑ፥ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ያለ ዕን​ቅ​ፋት ቅዱ​ሳን ትሆኑ ዘንድ፦ 11ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጽ​ድ​ቅን ፍሬ ትሞሉ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤
በቅ​ዱስ ጳው​ሎስ መታ​ሰር ወን​ጌል እንደ ተስ​ፋፋ
12ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ይህ የደ​ረ​ሰ​ብኝ በእ​ው​ነት ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ፋ​ፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ። 13#የሐዋ. 28፥30። ስለ ክር​ስ​ቶስ ስም መታ​ሰ​ሬም በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉና በሰው ሁሉ ዘንድ ታው​ቆ​አል። 14ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ብዙ​ዎቹ በእ​ስ​ራቴ ምክ​ን​ያት በጌታ ታመኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያለ ፍር​ሀት ጨክ​ነው ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ እጅግ ተደ​ፋ​ፈሩ።
15ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶች በቅ​ና​ታ​ቸ​ውና በክ​ር​ክ​ራ​ቸው፥ ሌሎ​ችም በበጎ ፈቃድ ስለ ክር​ስ​ቶስ ሊሰ​ብ​ኩና ሊያ​ስ​ተ​ምሩ የወ​ደዱ አሉ። 16በፍ​ቅር የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩም አሉ፤ ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር እንደ ተሾ​ምሁ ያው​ቃ​ሉና። 17በኵ​ራት ስለ ክር​ስ​ቶስ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ግን፥ ይህን አድ​ር​ገው በእ​ስ​ራቴ ላይ መከራ ሊጨ​ም​ሩ​ብኝ መስ​ሎ​አ​ቸው ነው እንጂ በእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ን​ነ​ትም አይ​ደ​ለም። 18ነገር ግን ምን አለ? በየ​ም​ክ​ን​ያቱ በእ​ው​ነ​ትም ቢሆን፥ በሐ​ሰ​ትም ቢሆን፥ ስለ ክር​ስ​ቶስ ይና​ገ​ራሉ፤ ሰው​ንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠ​ራሉ፤#“ሰው​ንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠ​ራሉ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በዚ​ህም ደስ ብሎ​ኛል፤ ወደ​ፊ​ትም ደስ ይለ​ኛል።
ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል መኖር
19እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ። 20በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል። 21እኔ በሕ​ይ​ወት ብኖ​ርም ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል ነው፤ ብሞ​ትም ዋጋ አለኝ። 22ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም። 23በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም። 24ደግ​ሞም ስለ እና​ንተ በሕ​ይ​ወተ ሥጋ ብኖር ይሻ​ላል። 25ይህ​ንም ዐውቄ ለማ​ደ​ጋ​ች​ሁና በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ለም​ታ​ገ​ኙት ደስታ እን​ደ​ም​ኖር አም​ና​ለሁ። 26ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።
27ነገር ግን ምና​ል​ባት የመ​ጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳል​ኖ​ርም ቢሆን በወ​ን​ጌል ሃይ​ማ​ኖት እየ​ተ​ጋ​ደ​ላ​ችሁ በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በአ​ንድ አካል ጸን​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራ​ችሁ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ገባ ይሁን። 28የእ​ነ​ርሱ ጥፋት፥ የእ​ና​ን​ተም ሕይ​ወት ይታ​ወቅ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙን ሰዎች በማ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ደ​ን​ግ​ጧ​ችሁ። 29ይህ​ንም ጸጋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልት​ቀ​በ​ሉም ነው እንጂ ልታ​ም​ኑ​በት ብቻ አይ​ደ​ለም። 30#የሐዋ. 16፥19-40። እን​ዲ​ሁም እኔን እን​ዳ​ያ​ች​ሁኝ፥ የእ​ኔ​ንም ነገር እንደ ሰማ​ችሁ ምን​ጊ​ዜም ተጋ​ደሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in