YouVersion Logo
Search Icon

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 4

4
በዲ​ያ​ብ​ሎስ ስለ መፈ​ተኑ
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመ​ልቶ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ተመ​ለሰ፤ መን​ፈ​ስም ወደ ምድረ በዳ ወሰ​ደው። 2አርባ መዓ​ል​ትና አርባ ሌሊት ከዲ​ያ​ብ​ሎስ ተፈ​ተነ፥ በእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች ምንም አል​በ​ላም፤ እነ​ዚ​ያም ቀኖች ከተ​ፈ​ጸሙ በኋላ ተራበ። 3ዲያ​ብ​ሎ​ስም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ከሆ​ን​ህስ ይህ ድን​ጋይ እን​ጀራ ይሁን በል” አለው። 4#ዘዳ. 8፥3። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ሰው የሚ​ኖ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወ​ጣው ቃል ነው እንጂ በእ​ን​ጀራ ብቻ አይ​ደ​ለም የሚል ተጽ​ፎ​አል” አለው። 5ዲያ​ብ​ሎ​ስም ወደ ረዥም ተራራ አወ​ጣው፤ የዓ​ለ​ምን መን​ግ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ በቅ​ፅ​በት አሳ​የው። 6ዲያ​ብ​ሎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ይህን ሁሉ ግዛት፥ ይህ​ንም ክብር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ለእኔ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ልና፤ ለወ​ደ​ድ​ሁ​ትም እሰ​ጠ​ዋ​ለ​ሁና። 7ስለ​ዚህ አንተ በፊቴ ብት​ሰ​ግ​ድ​ልኝ ይህ ሁሉ ለአ​ንተ ይሁ​ን​ልህ።” 8#ዘዳ. 6፥13። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ከኋ​ላዬ ሂድ #በግ​ሪ​ኩና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ትር​ጕም “ሰይ​ጣን ከኋ​ላዬ ሂድ” የሚ​ለ​ውን የሚ​ጽ​ፍም የማ​ይ​ጽ​ፍም አለ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ልት​ሰ​ግድ፥ እር​ሱ​ንም ብቻ ልታ​መ​ልክ ተጽ​ፎ​አል” አለው። 9ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወስዶ በቤተ መቅ​ደሱ የማ​ዕ​ዘን ጫፍ ላይ አቆ​መው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ከሆ​ን​ህስ አንተ ራስህ ወደ ታች መር ብለህ ውረድ። 10#መዝ. 90፥11። በመ​ን​ገ​ድህ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ትን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋል፤ 11#መዝ. 90፥12። እግ​ር​ህም በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከል በእ​ጃ​ቸው ያነ​ሡ​ሃል” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና። 12#ዘዳ. 6፥16። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ነው” ተብ​ሎ​አል አለው። 13ዲያ​ብ​ሎ​ስም በዚህ ሁሉ እር​ሱን መፈ​ታ​ተ​ኑን ከፈ​ጸመ በኋላ እስከ ጊዜው ከእ​ርሱ ተለየ።
ስለ መጀ​መ​ሪያ ትም​ህ​ርቱ
14ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል ተመ​ልሶ ወደ ገሊላ ሄደ፤ ዝና​ውም በሀ​ገሩ ሁሉ ተሰማ። 15በየ​ም​ኵ​ራ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር፤ ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ያደ​ንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።
በና​ዝ​ሬት ስለ ማስ​ተ​ማሩ
16ወደ አደ​ገ​በት ወደ ናዝ​ሬ​ትም ሄደ፤ በሰ​ን​በት ቀንም እን​ዳ​ስ​ለ​መደ ወደ ምኵ​ራብ ገባ፤ ሊያ​ነ​ብም ተነሣ። 17የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስ​ንም መጽ​ሐፍ ሰጡት፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም በገ​ለጠ ጊዜ እን​ዲህ የሚል የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ስፍራ አገኘ። 18“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ 19#ኢሳ. 61፥1-2። የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዓመት እሰ​ብክ ዘንድ ላከኝ።” 20መጽ​ሐ​ፉ​ንም አጥፎ ለተ​ላ​ላ​ኪው ሰጠ​ውና ተቀ​መጠ፤ በም​ኲ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ዐይ​ና​ቸ​ውን አት​ኲ​ረው ተመ​ለ​ከ​ቱት። 21እር​ሱም፥ “የዚህ የመ​ጽ​ሐፍ ነገር ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ ደረሰ፤ ተፈ​ጸ​መም” ይላ​ቸው ጀመር። 22ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር። 23እር​ሱም፥ “በውኑ ባለ መድ​ኀ​ኒት ራስ​ህን አድን፤ በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ሁሉ በዚ​ህም በሀ​ገ​ርህ ደግሞ አድ​ርግ ብላ​ችሁ ይህ​ችን ምሳሌ ትመ​ስ​ሉ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው። 24#ዮሐ. 4፥44። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነቢይ በሀ​ገሩ አይ​ከ​ብ​ርም። 25#1ነገ. 17፥8-16። እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ። 26ኤል​ያስ የሲ​ዶና ክፍል በም​ት​ሆን በስ​ራ​ጵታ ወደ​ም​ት​ኖር ወደ አን​ዲት መበ​ለት ሴት እንጂ ከእ​ነ​ዚህ ወደ አን​ዲቱ እን​ኳን አል​ተ​ላ​ከም። 27#2ነገ. 5፥1-14። በነ​ቢዩ በኤ​ል​ሳዕ ዘመ​ንም ብዙ ለም​ጻ​ሞች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከን​ዕ​ማን በቀር ከእ​ነ​ዚያ አንድ እን​ኳን አል​ነ​ጻም።”
28በም​ኵ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ይህን ሰም​ተው ተቈጡ። 29ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥ​ተው ከከ​ተማ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ ገፍ​ተ​ውም ይጥ​ሉት ዘንድ ከተ​ማ​ቸው ተሠ​ር​ታ​ባት ወደ ነበ​ረች ተራራ ጫፍ ወሰ​ዱት። 30እርሱ ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አልፎ ሄደ።
ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ስለ መሄዱ
31ወደ ገሊላ ከተ​ማም ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ወረደ፤ በሰ​ን​በ​ትም ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር። 32#ማቴ. 7፥28-29። አነ​ጋ​ገ​ሩም በት​እ​ዛዝ ነበ​ርና ትም​ህ​ር​ቱን ያደ​ንቁ ነበር።
ጋኔን የያ​ዘ​ውን ስለ ማዳኑ።
33በም​ኵ​ራ​ብም ርኩስ መን​ፈስ የያ​ዘው አንድ ሰው ነበር፤ በታ​ላቅ ቃልም ጮኾ፦ 34“የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለን? ያለ​ጊ​ዜ​አ​ችን ልታ​ጠ​ፋን መጣ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ሆይ፥ አንተ ማን እን​ደ​ሆ​ንህ ዐው​ቅ​ሃ​ለሁ” አለ። 35ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዝም በልና ከእ​ርሱ ውጣ” ብሎ ገሠ​ጸው፤ ጋኔ​ኑም በም​ኵ​ራቡ መካ​ከል ጣለ​ውና ከእ​ርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አል​ጐ​ዳ​ውም። 36ሁሉም ደነ​ገጡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተነ​ጋ​ገሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምን​ድን ነው? ክፉ​ዎ​ችን አጋ​ን​ንት በሥ​ል​ጣ​ንና በኀ​ይል ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፥ እነ​ር​ሱም ይወ​ጣ​ሉና።” 37ዝና​ውም በዙ​ሪ​ያዉ ባሉ መን​ደ​ሮች ሁሉ ወጣ፤ ተሰ​ማም።
ስለ ጴጥ​ሮስ አማ​ትና ስለ ሌሎ​ችም በሽ​ተ​ኞች መፈ​ወስ
38ከም​ኵ​ራ​ቡም ወጥቶ ወደ ስም​ዖን ቤት ገባ፤ የስ​ም​ዖን አማ​ትም በብ​ርቱ ንዳድ ታማ ነበ​ርና ስለ እር​ስዋ ነገ​ሩት። 39በአ​ጠ​ገ​ብ​ዋም ቁሞ ንዳ​ድ​ዋን ገሠ​ጸ​ውና ተዋት፤ ወዲ​ያ​ውም ተነ​ሥታ አገ​ለ​ገ​ለ​ቻ​ቸው። 40ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወ​ሳ​ቸው። 41ብዙ አጋ​ን​ን​ትም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ ነህ” እያ​ሉና እየ​ጮሁ ይወጡ ነበር፤ እር​ሱም ይገ​ሥ​ጻ​ቸው ነበር፤ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበ​ርና እን​ዲ​ና​ገሩ አይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸ​ውም ነበር።
42በነጋ ጊዜም ወጥቶ ወደ ምድረ በዳ ሄደ፤ ሕዝ​ቡም እየ​ፈ​ለ​ጉት ወደ እርሱ ሄዱ፤ አል​ፎ​አ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሄ​ድም አቆ​ሙት። 43እርሱ ግን፥ “ስለ​ዚህ ተል​ኬ​አ​ለ​ሁና ለሌ​ሎች ከተ​ሞች ደግሞ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወን​ጌል እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል” አላ​ቸው። 44በገ​ሊላ ምኲ​ራ​ቦ​ችም ይሰ​ብክ ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in