YouVersion Logo
Search Icon

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 23

23
ጌታ​ችን በጲ​ላ​ጦስ ፊት ስለ መቆሙ
1ሁሉም በሙሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጲላ​ጦስ ወሰ​ዱት። 2እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።” 3ጲላ​ጦ​ስም፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ እንደ ሆንሁ አንተ አልህ” አለው። 4ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው። 5ሕዝ​ቡም፥ “ከገ​ሊላ ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ድረስ በመ​ላው ይሁዳ እያ​ስ​ተ​ማረ ሕዝ​ቡን ያው​ካል” እያሉ አጽ​ን​ተው ጮኹ።
ጌታ​ችን በሄ​ሮ​ድስ ፊት ስለ መቆሙ
6ጲላ​ጦ​ስም “ገሊላ” ሲሉ ሰምቶ፤ ሰው​የዉ ገሊ​ላዊ እንደ ሆነ የገ​ሊ​ላን ሰዎች ጠየቀ። 7ከሄ​ሮ​ድስ ግዛ​ትም ውስጥ መሆ​ኑን ዐውቆ ወደ ሄሮ​ድስ ላከው፤ ሄሮ​ድስ በዚያ ወራት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበ​ርና። 8ሄሮ​ድ​ስም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ዜና​ውን ስለ​ሚ​ሰማ ከረ​ጅም ጊዜ ጀምሮ ሊያ​የው ይሻ ነበ​ርና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሊያይ ይመኝ ነበ​ርና። 9በብዙ ነገ​ርም መረ​መ​ረው፤ እርሱ ግን አን​ድስ እንኳ አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም። 10የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ቆመው በብዙ ያሳ​ጡት ነበር። 11ሄሮ​ድ​ስም ከሠ​ራ​ዊቱ ጋር አቃ​ለ​ለው፤ አፌ​ዘ​በ​ትም፤ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብ​ስም አል​ብሶ ወደ ጲላ​ጦስ መልሶ ሰደ​ደው። 12በዚ​ያም ቀን ሄሮ​ድ​ስና ጲላ​ጦስ ተስ​ማሙ፤ ቀድሞ ጥል ነበ​ራ​ቸ​ውና።
13ጲላ​ጦ​ስም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ች​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ጠራ​ቸው። 14እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ሰው ሕዝ​ብን ያሳ​ም​ፃል ብላ​ችሁ ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት፤ በፊ​ታ​ች​ሁም እነሆ፥ መረ​መ​ር​ሁት፤ ግን እና​ንተ ካቀ​ረ​ባ​ች​ሁት ክስ በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ዳች በደል የለም። 15ወደ ሄሮ​ድ​ስም ሰድ​ጃ​ችሁ ነበር፤ እር​ሱም ምንም ስላ​ላ​ገ​ኘ​በት ወደ እኛ መል​ሶ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ያደ​ረ​ገው ነገር የለም። 16እነሆ፥ እኔም እን​ግ​ዲህ ገርፌ ልተ​ወው” አለ።
በር​ባን ስለ መፈ​ታ​ቱና በጌታ ስለ መፈ​ረዱ
17በየ​በ​ዓ​ሉም ከእ​ስ​ረ​ኞች አንድ ሊፈ​ታ​ላ​ቸው ልማድ ነበር። 18ሁሉም በሙሉ፥ “ይህን አስ​ወ​ግ​ደው፥ ስቀ​ለ​ውም፥#“ስቀ​ለው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። በር​ባ​ንን ግን ፍታ​ልን” ብለው ጮሁ። 19ያ በር​ባን ግን በከ​ተማ ሁከት ያደ​ረ​ገና ነፍስ በመ​ግ​ደል የታ​ሰረ ነበር። 20ጲላ​ጦ​ስም ኢየ​ሱ​ስን ሊፈ​ታው ወድዶ፥ “ ኢየ​ሱ​ስን ልፈ​ታ​ላ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” ብሎ እንደ ገና ተና​ገ​ራ​ቸው። 21እነ​ርሱ ግን፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ይጮሁ ነበር። 22ጲላ​ጦ​ስም ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ፥ “ምን ክፉ ነገር አደ​ረገ? እነሆ፥ ለሞት የሚ​ያ​በቃ ምክ​ን​ያት አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም፤ እን​ኪ​ያስ ልግ​ረ​ፈ​ውና ልተ​ወው” አላ​ቸው። 23እን​ዲ​ሰ​ቅ​ሉ​ትም ቃላ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው እየ​ጮሁ ለመኑ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ውና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ድም​ፅም በረታ። 24ጲላ​ጦ​ስም የለ​መ​ኑት ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ፈረ​ደ​በት። 25ያን የለ​መ​ኑ​ትን፥ ነፍስ በመ​ግ​ደ​ልና ሁከት በማ​ድ​ረግ የታ​ሰ​ረ​ው​ንም ሰው ፈታ​ላ​ቸው፤ ኢየ​ሱ​ስን ግን ለፈ​ቃ​ዳ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።
ወደ መስ​ቀል ጕዞ
26በወ​ሰ​ዱ​ትም ጊዜ የቀ​ሬና ሰው ስም​ዖ​ንን ከዱር ሲመ​ለስ ያዙት፤ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱ​ስም በስ​ተ​ኋላ መስ​ቀ​ሉን አሸ​ከ​ሙት። 27ብዙ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ሴቶ​ችም “ዋይ ዋይ” እያሉ ያዝ​ኑ​ለ​ትና ያለ​ቅ​ሱ​ለት ነበሩ። 28ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጆች ሆይ፥ ለራ​ሳ​ች​ሁና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አል​ቅሱ እንጂ ለእ​ኔስ አታ​ል​ቅ​ሱ​ልኝ። 29መካ​ኖች፥ ያል​ወ​ለዱ ማኅ​ፀ​ኖ​ችና ያላ​ጠቡ ጡቶ​ችም የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው የሚ​ሉ​በት ወራት ይመ​ጣ​ልና። 30#ሆሴዕ 10፥8፤ ራእ. 6፥16። ያን​ጊ​ዜም ተራ​ሮ​ችን ‘በላ​ያ​ችን ውደቁ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ሰው​ሩን’ ይሉ​አ​ቸ​ዋል። 31በዚህ ርጥብ ዕን​ጨት እን​ዲህ ያደ​ረጉ በደ​ረ​ቁማ እን​ዴት ይሆን?”
ከወ​ን​በ​ዴ​ዎች ጋር ስለ መሰ​ቀሉ
32ሌሎች ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሊሰ​ቅሉ ወሰዱ። 33ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባ​ለው ቦታ በደ​ረሱ ጊዜም፥ በዚያ ሰቀ​ሉት፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎች አን​ዱን በቀኙ አን​ዱ​ንም በግ​ራው ሰቀሉ። 34#መዝ. 21፥18። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ። 35#መዝ. 21፥7። ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር። 36#መዝ. 68፥21። ጭፍ​ሮ​ችም ይዘ​ብ​ቱ​በት ነበር፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው ሆም​ጣጤ አመ​ጡ​ለት። 37እን​ዲ​ህም ይሉት ነበር፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ከሆ​ን​ህስ ራስ​ህን አድን።” 38በራ​ስ​ጌ​ውም ደብ​ዳቤ ጻፉ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በሮ​ማ​ይ​ስጥ፥ በጽ​ር​ዕና በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ሆኖ “የአ​ይ​ሁድ ንጉ​ሣ​ቸው ይህ ነው” የሚል ነበር።
ስለ ሁለቱ ወን​በ​ዴ​ዎች
39አብ​ረው ተሰ​ቅ​ለው ከነ​በ​ሩት አንዱ ወን​በዴ፥ “አን​ተስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ንህ ራስ​ህን አድን፤ እኛ​ንም አድ​ነን” ብሎ ተሳ​ደበ። 40ጓደ​ኛ​ውም መልሶ ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ ሳለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን#“አም​ላ​ክ​ህን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አት​ፈ​ራ​ው​ምን? 41በእ​ኛስ በሚ​ገባ ተፈ​ር​ዶ​ብ​ናል፤ እንደ ሥራ​ች​ንም ፍዳ​ች​ንን ተቀ​በ​ልን፤ ይህ ግን ምንም የሠ​ራው ክፉ ሥራ የለም።” 42ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው። 43ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ በገ​ነት ከእኔ ጋር ትሆ​ና​ለህ።”
ጌታ ስለ መሞ​ቱና ስለ ተአ​ም​ራቱ
44ቀትር በሆነ ጊዜም በስ​ድ​ስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረ​ስም ዓለም ሁሉ #በግ​ሪኩ “ምድር ሁሉ” ይላል። ጨለማ ሆነ። 45#ዘፀ. 26፥31-33። ፀሐ​ዩም በጨ​ለመ ጊዜ የቤተ መቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ከላይ እስከ ታች#“ከላይ እስከ ታች” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ከመ​ካ​ከሉ ተቀ​ደደ። 46#መዝ. 30፥5። ያን​ጊ​ዜም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍ​ሴን በአ​ንተ እጅ አደራ እሰ​ጣ​ለሁ” ብሎ ጮኸ፤ ይህ​ንም ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ። 47የመቶ አለ​ቃ​ውም የሆ​ነ​ውን ነገር አይቶ፥ “ይህ ሰው በእ​ው​ነት ጻድቅ ነበረ”ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው። 48ይህ​ንም ለማ​የት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ የሆ​ነ​ውን ባዩ ጊዜ፥ ደረ​ታ​ቸ​ውን እየ​መቱ ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ። 49#ሉቃ. 8፥2-3። የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉና ከገ​ሊላ ጀምሮ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሴቶች በሩቁ ቆመው ይህን ያዩ ነበር።
ጌታ ስለ መቀ​በሩ
50እነሆ፥ በጎና ጻድቅ ሰው፥ የሸ​ንጎ አማ​ካ​ሪም የሆነ ዮሴፍ የሚ​ባል ሰው መጣ። 51እር​ሱም በአ​ይ​ሁድ በም​ክ​ራ​ቸ​ውና በሥ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ረም ነበር፤ ሀገ​ሩም የይ​ሁዳ ዕጣ የሚ​ሆን አር​ማ​ት​ያስ ነበር፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ተስፋ ያደ​ርግ ነበር። 52ወደ ጲላ​ጦ​ስም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ለመነ። 53ሥጋ​ው​ንም አው​ርዶ በበ​ፍታ ገነ​ዘው፤ ማንም ባል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት፥ ከድ​ን​ጋ​ይም በተ​ፈ​ለ​ፈለ መቃ​ብር ቀበ​ረው፤ ታላቅ ድን​ጋ​ይም አን​ከ​ባ​ልሎ መቃ​ብ​ሩን ገጥሞ ሄደ።#“ታላቅ ድን​ጋ​ይም አን​ከ​ባ​ልሎ መቃ​ብ​ሩን ገጥሞ ሄደ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። 54ያም ቀን የሰ​ን​በት መግ​ቢያ ዐርብ ነበር። 55ከገ​ሊ​ላም ከእ​ርሱ ጋር የመጡ ሁለት#በግ​ሪኩ “ሁለት” አይ​ልም። ሴቶች ተከ​ት​ለው፥ መቃ​ብ​ሩን፥ ሥጋ​ው​ንም እን​ዴት እን​ዳ​ኖ​ሩት አዩ። ተመ​ል​ሰ​ውም ሽቱና ዘይት አዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት አል​ሄ​ዱም፤ ሕጋ​ቸው እን​ዲህ ነበ​ርና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in