YouVersion Logo
Search Icon

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 2

2
ስለ ሕዝብ ቈጠራ
1በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈ​ጠር ዘንድ ከአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ቄሣር ትእ​ዛዝ ወጣ። 2ቄሬ​ኔ​ዎስ ለሶ​ርያ መስ​ፍን በነ​በረ ጊዜ ይህ የመ​ጀ​መ​ርያ ቈጠራ ሆነ። 3ሰው ሁሉ ሊቈ​ጠር ወደ​የ​ከ​ተ​ማው ሄደ። 4ዮሴ​ፍም ከገ​ሊላ አው​ራጃ ከና​ዝ​ሬት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ቤተ ልሔም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ዳዊት ከተማ ወጣ፤ እርሱ ከዳ​ዊት ሀገ​ርና#በግ​ሪኩ “ከዳ​ዊት ቤትና” ይላል። ከዘ​መ​ዶ​ቹም ወገን ነበ​ርና። 5ፀንሳ ሳለች ከእ​ጮ​ኛው ከማ​ር​ያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ሄደ።
ስለ ጌታ​ችን መወ​ለድ
6በዚያ ሳሉም የም​ት​ወ​ል​ድ​በት ቀን ደረሰ። 7የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም ወለ​ደች፤ አውራ ጣቱ​ንም አሰ​ረ​ችው፤ #“አውራ ጣቱ​ንም አሰ​ረ​ችው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በጨ​ር​ቅም ጠቀ​ለ​ለ​ችው፤ በበ​ረ​ትም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ በማ​ደ​ር​ያ​ቸው ቦታ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና። 8በዚያ ሀገር እረ​ኞች ነበሩ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ተግ​ተው መን​ጋ​ቸ​ውን ይጠ​ብቁ ነበር። 9እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በዙ​ሪ​ያ​ቸው አበራ፤ ታላቅ ፍር​ሀ​ት​ንም ፈሩ። 10መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ለእ​ና​ን​ተና ለሕ​ዝቡ ሁሉ ደስታ የሚ​ሆን ታላቅ የም​ሥ​ራች እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለ​ሁና አት​ፍሩ። 11እነሆ፥ ዛሬ በዳ​ዊት ከተማ መድ​ኅን ተወ​ል​ዶ​ላ​ች​ኋል፤ ይኸ​ውም ቡሩክ ጌታ ክር​ስ​ቶስ ነው። 12ለእ​ና​ን​ተም ምል​ክቱ እን​ዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥#“አውራ ጣቱን ታስሮ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በጨ​ር​ቅም ተጠ​ቅ​ልሎ በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ ታገ​ኛ​ላ​ቸሁ።” 13ድን​ገ​ትም ከዚያ መል​አክ ጋር ብዙ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ መጡ። 14“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።
15ከዚ​ህም በኋላ መላ​እ​ክት ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በዐ​ረጉ ጊዜ እነ​ዚያ እረ​ኞች ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “እስከ ቤተ ልሔም እን​ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የገ​ለ​ጠ​ል​ንን ይህን ነገር እን​ወቅ” አሉ። 16ፈጥ​ነ​ውም ሄዱ፤ ማር​ያ​ም​ንና ዮሴ​ፍን አገ​ኙ​አ​ቸው፤ ሕፃ​ኑ​ንም በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ አገ​ኙት። 17በአ​ዩም ጊዜ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ስለ​ዚህ ሕፃን እንደ ሆነ ዐው​ቀው አወሩ። 18የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እረ​ኞቹ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸ​ውን አደ​ነቁ። 19ማር​ያም ግን ይህን ሁሉ ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር። 20እረ​ኞ​ችም እንደ ነገ​ሩ​አ​ቸው ባዩ​ትና በሰ​ሙት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በ​ሩና እያ​መ​ሰ​ገኑ ተመ​ለሱ።
ስለ ሕፃኑ መገ​ዘ​ርና ወደ ቤተ መቅ​ደስ መግ​ባት
21 # ዘሌ. 12፥3፤ ሉቃ. 1፥31። ስም​ንት ቀን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜም ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት ወሰ​ዱት፤ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ሳት​ፀ​ን​ሰው መል​አኩ እን​ዳ​ወ​ጣ​ለ​ትም ስሙን ኢየ​ሱስ አሉት። 22#ዘሌ. 12፥6-8። የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እንደ ሙሴ ሕግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ሙት ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት። 23#ዘፀ. 13፥2፤ 12። “በኵር ሆኖ የሚ​ወ​ለድ ወንድ ልጅ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይባ​ላል” ተብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እንደ ተጻፈ፥ 24በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ስለ እርሱ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ቡ​ለት ዘንድ።
ስለ አረ​ጋ​ዊው ስም​ዖን
25በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስሙ ስም​ዖን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ጻድ​ቅና ደግ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ደስ​ታ​ቸ​ውን ያይ ዘንድ ተስፋ ያደ​ርግ ነበር፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስም ያደ​ረ​በት ነበር። 26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መሲሕ ሳያይ እን​ደ​ማ​ይ​ሞት መን​ፈስ ቅዱስ ገል​ጦ​ለት ነበር። 27መን​ፈ​ስም ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወሰ​ደው፤ ዘመ​ዶ​ቹም በሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ያደ​ር​ጉ​ለት ዘንድ ሕፃ​ኑን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ቤተ መቅ​ደስ በአ​ገ​ቡት ጊዜ፥ 28እርሱ ደግሞ ተቀ​ብሎ በክ​ንዱ ታቀ​ፈው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነው። 29እን​ዲ​ህም አለ፤ “አቤቱ፥ እንደ አዘ​ዝህ ዛሬ ባር​ያ​ህን በሰ​ላም ታሰ​ና​ብ​ተ​ዋ​ለህ። 30ዐይ​ኖች ትድ​ግ​ና​ህን አይ​ተ​ዋ​ልና። 31በወ​ገ​ንህ ሁሉ ፊት ያዘ​ጋ​ጀ​ኸ​ውን፥ 32ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃ​ንን፥ ለወ​ገ​ንህ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ክብ​ርን ትገ​ልጥ ዘንድ።” 33ዮሴ​ፍና እናቱ ግን በእ​ርሱ ላይ ስለ​ሚ​ና​ገ​ረው ያደ​ንቁ ነበር። 34ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤ 35ባንቺ ግን በል​ብሽ ፍላጻ ይገ​ባል፤ የብ​ዙ​ዎ​ቹን ዐሳብ ይገ​ልጥ ዘንድ።”
ስለ ነቢ​ይቱ ሐና
36ከአ​ሴር ወገን የም​ት​ሆን የፋ​ኑ​ኤል ልጅ ሐና የም​ት​ባል ነቢ​ይት ነበ​ረች፤ አር​ጅ​ታም ነበር፤ ከድ​ን​ግ​ል​ና​ዋም በኋላ ከባል ጋር ሰባት ዓመት ኖረች። 37ሰማ​ንያ አራት ዓመ​ትም መበ​ለት ሆና ኖረች፤ በጾ​ምና በጸ​ሎ​ትም እያ​ገ​ለ​ገ​ለች፥ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቤተ መቅ​ደስ አት​ወ​ጣም ነበር። 38ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ድኅ​ነት ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተና​ገ​ረች።
39 # ማቴ. 2፥23። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ ከተ​ማ​ቸው ወደ ናዝ​ሬት ተመ​ለሱ። 40ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።
በሊ​ቃ​ው​ንት መካ​ከል ስለ መገ​ኘቱ
41 # ዘፀ. 12፥1-27፤ ዘዳ. 16፥1-8። ዘመ​ዶ​ቹም በየ​ዓ​መቱ ለፋ​ሲካ በዓል ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄዱ ነበር። 42ዐሥራ ሁለት ዓመ​ትም በሞ​ላው ጊዜ እንደ አስ​ለ​መዱ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለበ​ዓል ወጡ። 43#ግሪኩ “ቀኖ​ቹ​ንም ከፈ​ጸሙ በኋላ” ይላል።ሥራ​ቸ​ው​ንም ጨር​ሰው ተመ​ለሱ፤ ሕፃኑ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴ​ፍና እና​ቱም አላ​ወ​ቁም ነበር። 44በመ​ን​ገ​ድም ከሰ​ዎች ጋር ያለ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ ያንድ ቀን መን​ገ​ድ​ንም ከሄዱ በኋላ ዕለ​ቱን ከዘ​መ​ዶቹ፥ ከሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ዘንድ ፈለ​ጉት። 45ባላ​ገ​ኙ​ትም ጊዜ እየ​ፈ​ለ​ጉት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ። 46ከዚ​ህም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤተ መቅ​ደስ በሊ​ቃ​ው​ንት መካ​ከል ተቀ​ምጦ ሲሰ​ማ​ቸ​ውና ሲጠ​ይ​ቃ​ቸው አገ​ኙት። 47የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አስ​ተ​ዋ​ይ​ነ​ቱ​ንና አመ​ላ​ለ​ሱን ያደ​ንቁ ነበር። 48በአ​ዩ​ትም ጊዜ ደነ​ገጡ፤ እና​ቱም፥ “ልጄ፥ ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግ​ኸን? እነሆ አባ​ት​ህም፥#“አባት” የተ​ባለ አሳ​ዳ​ጊው ስለ​ሆነ ነው። እኔም ስን​ፈ​ል​ግህ ደከ​ምን” አለ​ችው። 49እር​ሱም፥ “ለምን ትፈ​ል​ጉ​ኛ​ላ​ችሁ? በአ​ባቴ ቤት ልኖር እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ አላ​ወ​ቃ​ች​ሁ​ምን?” አላ​ቸው። 50እነ​ርሱ ግን የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃል አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም። 51ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝ​ሬት ወረደ፤ ይታ​ዘ​ዝ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው#“ታኖ​ረው ነበር” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ነበር። 52#1ሳሙ. 2፥26፤ ምሳ. 3፥4። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ፥ በሰ​ውም ዘንድ፥ በጥ​በ​ብና በአ​ካል በሞ​ገ​ስም አደገ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in