YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 9

9
አሮን መሥ​ዋ​ዕት ስለ ማቅ​ረቡ
1በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠራ። 2ሙሴም አሮ​ንን አለው፥ “ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋው እን​ቦ​ሳ​ውን፥ ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አው​ራ​ውን በግ#ዕብ. “ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን” ይላል። ወስ​ደህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፦ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ልን፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ዓመት የሆ​ና​ቸ​ውን ጥጃና ጠቦ​ትን፥ 4ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ንና አውራ በግን፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ልና ብለህ ንገ​ራ​ቸው።” 5ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ። 6ሙሴም፥ “ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ቃል ይህ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋል” አለ። 7ሙሴም አሮ​ንን፥ “ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀር​በህ የኀ​ጢ​አ​ት​ህን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን ሠዋ፤ ለራ​ስ​ህና ለወ​ገ​ንህ አስ​ተ​ስ​ርይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘዘ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቅ​ርብ፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም” አለው።
8አሮ​ንም ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ጥጃ አረደ። 9የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ስቡ​ንና ኵላ​ሊ​ቶ​ቹን፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ። 11ሥጋ​ው​ንና ቍር​በ​ቱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።
12የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አረደ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ረጨው። 13የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በየ​ብ​ልቱ፥ ራሱ​ንም አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመ​ረው። 14የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ላይ ጨመ​ረው።
15ከዚ​ህም በኋላ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ፍየል ወስዶ አረ​ደው፤ አነ​ጻ​ውም፤ እንደ ፊተ​ኛ​ውም ለየው። 16የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም አደ​ረ​ገው። 17የስ​ን​ዴ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ ከእ​ር​ሱም እፍኝ ሙሉ ወስዶ በጥ​ዋት ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመ​ረው።
18ስለ ሕዝቡ የሆ​ነ​ውን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት፥ በሬ​ው​ንና አው​ራ​ውን በግ አረደ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አመ​ጡ​ለት፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ ረጨው፤ 19የበ​ሬ​ው​ንና የአ​ው​ራ​ው​ንም በግ ስብ፥ ላቱ​ንም፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ ሁለ​ቱን ኵላ​ሊ​ቶ​ቹ​ንም፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ አመ​ጡ​ለት። 20ስቡ​ንም በፍ​ር​ም​ባ​ዎቹ ላይ አኖረ፤ ስቡ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤#ዕብ. “አቃ​ጠለ” ይላል። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አሮን ፍር​ም​ባ​ዎ​ቹ​ንና ቀኝ ወር​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለየ።#ግእዝ “ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕድሉ ነውና አሮን ቀኝ ወር​ቹ​ንና ፍር​ም​ባ​ውን ለየ” ይላል።
22አሮ​ንም እጆ​ቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ የኀ​ጢ​አ​ቱን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ። 23ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ገቡ፤ ወጡም፤ ሕዝ​ቡ​ንም ባረኩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለሕ​ዝቡ ሁሉ ተገ​ለጠ። 24እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ስቡ​ንም በላ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው ተደ​ነቁ፤ በግ​ም​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in